Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢሰመኮ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ካሉበት ‹‹ከሕግ ውጪ›› የሆነ እስር በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠየቀ

ኢሰመኮ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ካሉበት ‹‹ከሕግ ውጪ›› የሆነ እስር በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠየቀ

ቀን:

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መንግሥት ከመገናኛ ብዙኃን ሕግ ‹‹ውጪ›› ያሰራቸውን 17 ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞች በሙሉ በአስቸኳይ እንዲለቅ ጠየቀ፡፡

ከመገናኛ ብዙኃን ሕጉ በተቃራኒ ታሳሪዎች ወደ ችሎት ከመቅረባቸው በፊት ረዘም ላለ ጊዜ የሚታሰሩ መሆኑ፣ የእስር ቦታ አለመገለጽና መደበኛ ባልሆኑ የማቆያ ቦታዎች መታሰር ሁኔታውን ማባባሳቸውንም ኮሚሽኑ ዓርብ ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡።

መግለጫው የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝና የኢትዮ ፎረም ሚድያ አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስን ጨምሮ 16 ጋዜጠኛና የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞች መታሰራቸውን አስታውቋል፡፡ ኢሰመኮ፣ ከመግለጫው መውጣት በኋላ የፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ የምትሠራው ጋዜጠኛ ሰቦንቱ አሕመድ መታሰሯን በማረጋገጡ ቁጥሩ ወደ 17 ማደጉን የኮሚሽኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ታሪኳ ደሳለኝ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር)፣ ‹‹የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎቹ እስር የተፈጸመው ከመገናኛ ብዙኃን ሕጉ በተፃራሪ መሆኑና የሚያስከትለው መዘዝ ከመገናኛ ብዙኃን ምኅዳርና ከሐሳብ ነፃነት የዘለለ መሆኑ አስደንጋጭ ነው፤›› ማለታቸው በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል፡፡

በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት ተፈጽሟል ተብሎ የሚጠቀስ የትኛውም ጥፋት ባለፈው ዓመት የፀደቀውን የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እንደሚጥስ የገለጹት ኮሚሽነር ዳንኤል (ዶ/ር)፣ አዋጁ በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው የሚከሰሱ ሰዎች ላይ የሚደረግን ከችሎት በፊት የሆነ እስርን እንደሚከለክል ተናግረዋል፡፡

ዳንኤል (ዶ/ር)፣ መንግሥት ሁሉንም ጋዜጠኞችና የመገናኝ ብዙኃን ሠራተኞች በአስቸኳይ እንዲለቅ ጠይቀዋል፡፡ ኮሚሽኑ ሁኔታውን መከታተሉን እንደሚቀጥልም በመግለጫው ላይ ተገልጿል፡፡

ኢሰመኮ መታሰራቸውን ከገለጻቸው ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞች ውስጥ ሦስት ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ጋዜጠኞች፣ አምስት የአሻራ ሚድያ ዩትዩብ ቻናል ጋዜጠኞች፣ ሠራተኞችና የንስር ኢንተርናሽናል ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዩትዩብ ቻናል አራት ሠራተኞች ይገኙበታል፡፡

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች የሆነው ሲፒጄ ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በተመሳሳይ 11 ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞች መታሰራቸውን ገልጾ ነበር፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናትም በአስቸኳይ ሁሉንም ጋዜጠኞች የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞች ያለ ምንም ክስ እንዲለቅና የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የዘፈቀደ እስራት፣ የጭቆናና የሳንሱር ፍርኃት ሳያድርባቸው መሥራት የሚችሉ መሆኑን እንዲያረጋግጡ ጠይቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...