Monday, December 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በኢትዮጵያ 43 በመቶ የሚሆነው የሚታረስ መሬት በአሲዳማነት መጠቃቱ  ተገለጸ

ተዛማጅ ፅሁፎች

7 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ሙሉ ለሙሉ ምርት መስጠት አይችልም

ለኖራ ግዥ ተመድቦ የነበረውን 800 ሚሊየን ብር ማግኘት አልተቻለም በምስጋናው ፈንታው

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ለምርት ከሚውለው የእርሻ መሬት ውስጥ 43 በመቶ የሚሆነው መሬት በአሲድ የተጠቃ መሆኑን፣ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ ለእርሻ የሚውለው መሬት 15 ሚሊዮን ሔክታር ነው ያሉት በግብርና ሚኒስቴር የአፈር ለምነት ማሻሻያ ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ሰለሞን፣ ከዚህም ውስጥ 43 በመቶ የሚሆነው በአሲዳማነት የተጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡

ወደ አሲዳማነት የተቀየረው የእርሻ መሬት በአጠቃላይ 6.5 ሚሊዮን ሔክታር መሆኑን፣ ከዚህም ውስጥ 2.8 ሚሊዮን ሔክታሩ ወደ መካከለኛ አሲዳማነት የገባና በከፊል ምርት መስጠት የሚችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ቀሪው 3.7 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ደግሞ ከባድ አሲዳማነት ውስጥ የሚገኝና ሙሉ በሙሉ ምንም ዓይነት ምርት መስጠት እንደማይችል ተናግረዋል።

የአፈር አሲዳማነት ለሰብል የሚያስፈልጉ ንጥረ ነገሮች ሲያልቁና ለሰብል ጎጂ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ሲጨምሩ የሚከሰት መሆኑን፣ በሰብል ምርታማነት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደሚያደርግ የሚገልጹት አቶ ተፈራ፣ ለዚህም የእርሻ መሬትን መንከባከብ እንደሚጠይቅ አብራርተዋል።

በተለይም አርሶ አደሮችም ሆኑ በእርሻ ሥራ የተሰማሩ ባለሀብቶች የእርሻ መሬቶችን እንዲንከባከቡ የሚያስገድድ ፖሊሲ ሊኖር እንደሚገባ አክለዋል።

አሲዳማነትን ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚውለው ኖራ አገር ውስጥ እንደሚመረት፣ ካለው ፍላጎት አንፃር ግን ከፍተኛ እጥረት እንዳለ ተናግረዋል። በአሲዳማነት የተጠቃን አንድ ሔክታር መሬት ለማከም 30 ኩንታል ኖራ እንደሚጠይቅ፣ ወደፊት እየጨመረ ከሚሄደው የመሬት አሲዳማነት አኳያም ክፍተት መኖሩን ገልጸዋል።

በ2014 ዓ.ም. ለኖራ ግዥ የተመደበውን 800 ሚሊዮን ብር ማግኘት አለመቻሉን ገልጸው፣ ለዚህም የማዳበሪያ ዋጋ መወደድ በቂ በጀት እንዳይገኝ አድርጓል ብለዋል።

በኖራ የታከመ መሬት ቀድሞ ከነበረው ምርታማነት 300 ፐርሰንት የተሻለ ምርት መስጠት እንደሚችል የገለጹት አቶ ተፈራ፣ ነገር ግን በመንግሥት የሚመረተው ኖራ በቂ ባለመሆኑ የግል ባለሀብቶች እንዲያመርቱ ፍላጎት መኖሩን ተናግረዋል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች