Monday, July 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየ‹‹አይሠለጥንብኝም›› ወጣቱን ከሱስ የማውጣት መንገድ

የ‹‹አይሠለጥንብኝም›› ወጣቱን ከሱስ የማውጣት መንገድ

ቀን:

ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ዕድገቷ ወደፊት አንድ ዕርምጃ ከፍ እንዲል መንግሥት ወጣቶች ላይ መሥራት እንዳለበት ይታመናል፡፡ በተለይም ከሥር መሠረቱ በሥነ ምግባር የታነጹ ዜጎችን ለማፍራት ወጥ የሆነ አሠራር አለመኖሩና መንግሥት ዘርፉ ላይ ትኩረት ሰጥቶ አለመሥራቱን በመግለጽ ይህ እንዲስተካከልና ሁሉም የኃላፊነቱን እንዲወጣ ምሁራንም ሆኑ ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተለያዩ መድረኮች ላይ ሲያነሱ ይደመጣል፡፡

ችግሩን ለመፍታት ዘርፉ ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለማሳየትና በከተማዋ ከመጠን በላይ በሱስ ውስጥ ተደብቀው የሚገኙ ወጣቶችን ከገቡበት ሱስ ለማውጣት ‹‹አይሠለጥንብኝም ፀረ ሱስ ማኅበራዊ አገልግሎት››፣ ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር ለመሥራት  የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

የአይሠለጥንብኝም ፀረ ሱስ ማኅበራዊ አገልግሎት መሥራች ዳይሬክተርና መጋቢ ቢንያም አዱኛ እንደገለጹት፣ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ወጣቶች በተለያየ ሱስ ተጠምደዋል፡፡ እነዚህን ወጣቶች ከተጠመዱበት ሱስ ለማውጣት ተቋሙ ከአጋር ድርጅቶች ጋር እየሠራ ሲሆን፣ በዚህም በርካታ ወጣቶች እየሠለጠኑ ወደ ሥራ እየገቡ ነው፡፡

በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ከሦስት ሺሕ በላይ ዜጎችን ተደራሽ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን የተናገሩት ዳይሬክተሩ፣ በቀጣይም በተለያዩ ምዕራፎች አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን አክለዋል፡፡

አገልግሎቱን በትምህርት ቤቶች፣ በጎዳና ላይ የሚገኙ ወጣቶችና ሌሎች ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገልጸው፣ ለዚህም በሕክምና ባለሙያዎች በመታገዝ ግንዛቤ አገልግሎቱ እንደሚሠጥ ተናግረዋል፡፡  

በሥልጠናው የተሳተፉ ወጣቶች የሱስ ተጎጂ እንዳይሆኑ ሥልጠና እንደተሰጣቸና ራሳቸውን የሚመዝኑበት አሠራር መዘርጋቱን ጠቁመዋል፡፡

አገልግሎቱ በሚሰጥበት ወቅት የሥነ አዕምሮ ባለሙያዎች፣ የሥነ ልቦናና የማኅበራዊ ልማት ባለሙያዎች በተለያዩ ዘርፎች የማማከር ሙያ ያላቸው ግለሰቦች፣ አርቲስቶች፣ የእምነት አባቶች እንዲሁም የተለያዩ የማኅበረሰቡን ክፍሎች በማካተት የሚሠራ ይሆናል ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማም ሆነ በተለያዩ የክልል ከተሞች የሚገኙ ወጣቶች ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከሱስ ጋር ተያይዞ የሚታየውን የባህሪ ለውጥ ለመቅረፍ ወጣቶች ላይ መሥራት ያስፈልጋል ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥበቡ በቀለ ናቸው፡፡

የከተማዋን ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማኅበራዊ ዳራ ከፍ ለማድረግ ወጣቶች ላይ መሥራት እንደሚያስፈልግ የተናገሩት ኃላፊው፣ ችግሩን ለመቅረፍ ቢሮው ከአጋር ድርጅቶች ጋር እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያም ከፍተኛ ቁጥር የያዙት ወጣቶች መሆናቸውን፣ እነዚህም ወጣቶች ከአጉል ሱስ ተላቀው ያላቸውን ክህሎት ሥራ ላይ እንዲያውሉት መንግሥትም ሆነ ባለሀብቶች ትልቁን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...