Thursday, July 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልኢትዮጵያ ያቀደችው ክፍለ አኅጉራዊው የጥበባትና የባህል ፌስቲቫል

ኢትዮጵያ ያቀደችው ክፍለ አኅጉራዊው የጥበባትና የባህል ፌስቲቫል

ቀን:

በአፍሪካ ፖለቲካዊ መዲናነት የምትታወቀው አዲስ አበባ በአኅጉርም ሆነ በክፍለ አኅጉር ደረጃ የጥበባትና የባህል ፌስቲቫል አዘጋጅነት ለምን ሳትተጋ ቆየች የሚል አስተያየት ከዘርፉ ባለሙያዎች በየጊዜው ሲሰማ የቆየ ነው፡፡

ሰሞኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የምሥራቅ አፍሪካ አገሮችን የሚያሳትፍ የጥበባትና የባህል ፌስቲቫል በመጪው ሰኔ ወር ለማካሄድ አቅጃለሁ ብሏል፡፡  

ሚኒስቴሩ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ፌስቲቫል ከሰኔ 7 እስከ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ እንደሚሆን፣ ይህንንም ታላቅ ቀጣናዊ ሁነት ለማሳካት ከአጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማካሄዱን አስታውቋል፡፡

በፕሬስ መግለጫው ላይ እንደተመለከተው፣ የጥበባትና የባህል ፌስቲቫሉ የሙዚቃ፣ የፊልም፣ ሥዕልና ቅርፃ ቅርፅን፣ የመጻሕፍትና የዕደ ጥበባት ዓውደ ርዕይ፣ የሲምፖዚየምና የስፖርት ፌስቲቫሎችን በውስጡ የያዘ ነው፡፡

ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ባስተላለፉት መልዕክት ፌስቲቫሉ የኢትዮጵያን ገጽታ በማስተዋወቅ፣ የቀጣናውን አገሮች ሕዝቦች በማስተሳሰር፣ በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ተጠቃሚ እንድንሆን የሚያደርገን በመሆኑ አጋሮችና ባለድርሻዎች አብረን እንሥራ በማለት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

‹‹የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች የጥበብና የባህል ቋት ናቸው፤›› የሚል ኃይለ ሐሳብ ያንፀባረቁት በምክክሩ መድረክ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንን ናቸው፡፡ አያይዘውም ቀጣናውንም በአትሌቲክስ ብቻ ሳይሆን በጥበባትና በባህል ፌስቲቫልም የሚታወቅ እናደርገዋለን ብለዋል፡፡

ባለፈው ወር መገባደጃ የጥበባትና የባህል ፌስቲቫል የዝግጅት ሒደትና ቀጣይ መከናወን በሚገባቸው ዓበይት ተግባት ላይ መቀመጫቸውን በኢትዮጵያ ካደረጉ የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች አምባሳደሮችና ተወካዮች ጋር ውይይት መካሄዱን የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ ገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...