ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ፣ በዳግማዊ ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም. በተመረቀበት ዕለት ከተናገሩት የተወሰደ፡፡ ሰው በሚያውቀው በተማረበት በርካታ ድንቅ ሥራ ሊሠራ እንደሚችል አይቻለሁ፣ ባየሁትም ነገር ተደስቻለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሆስፒታሎች ንፁህና ለሁሉም ሰው የሚስማማ መሆን እንዳለባቸው ጠቁመው፣ ለውበት ለአረንጓዴነት ለንፅህና ቢያንስ የገባን ሰዎች እንተባበር ብለዋል፡፡