Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየአውሮፓ ኅብረት ከሩሲያ በባህር የሚገባ ነዳጅ ላይ የጣለው ማዕቀብ በዓመቱ መጨረሻ ሊተገብር...

የአውሮፓ ኅብረት ከሩሲያ በባህር የሚገባ ነዳጅ ላይ የጣለው ማዕቀብ በዓመቱ መጨረሻ ሊተገብር ነው

ቀን:

የአውሮፓ ኅብረት አባል አገሮች ከሩሲያ በባህር በሚያስገቡት የነዳጅ ዘይት ላይ ማዕቀብ ለመጣል የተስማሙ ሲሆን፣ ይህንንም በየዓመቱ መጨረሻ ተግባራዊ ለማድረግ መስማማታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ኅብረቱ ከዚህ ቀደም የሩሲያ ዩክሬን ጦርነትን አስመልክቶ በሩሲያ ላይ ማዕቀቦችን ለመጣል ሲያደርግ የነበረውን ምክክር ለማጠናከርና ውሳኔ ለመስጠት ግንቦት 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፣ ኅብረቱ እ.ኤ.አ. በ2023፣ 90 በመቶ ያህሉን ከሩሲያ የሚገባ ነዳጅ ዘይትን ለማገድ ማቀዱንም አስታውቋል፡፡

የኅብረቱ አባል አገሮች ከዚህ በፊት በነበራቸው ውይይት፣ ከሩሲያ በሚያስገቡት ነዳጅ ዘይትና ጋዝ ላይ ሙሉ ለሙሉ ማዕቀብ መጣል መልሶ ራሳቸውን እንደሚጎዳ በመግለጽ፣ ማዕቀቡን ቀስ በቀስ ተግባራዊ ማድረግ በሚለው ሐሳብ ላይ በአብዛኛው መስማማታቸው ይታወሳል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በተለይ ሃንጋሪ ከሩሲያ የምታስገባው ነዳጅ ዘይት ላይ ማዕቀብ መጣል አገሪቷን ላልተገባ ቀውስ እንደሚዳርግ በመግለጽ ማዕቀቡን እንደማትቀበል አስታውቃ ነበር፡፡ ሃንጋሪ ባነሳችው ከባድ ተቃውሞም ምክንያት የአውሮፓ ኅብረት ዓመቱ መጨረሻ ላይ በሩሲያ ነዳጅ ዘይት ላይ ለመጣል ያሰበውን ማዕቀብ በባህር በሚገባው ላይ ብቻ እንዲያደርግ ተገዷል፡፡

ሩሲያም በባህር ከምትልከው ነዳጅ ዘይት ሁለት ሦስተኛ ያህሉ ማዕቀቡ ያርፍበታል፡፡ ነገር ግን በቱቦ የሚላከውን ነዳጅ ዘይት ማዕቀቡ ለጊዜው አይመለከትም፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ፖላንድና ጀርመን ከሩሲያ በቱቦ የሚያስገቡትን ነዳጅ ዘይት ለማቆም ቃል ገብተዋል፡፡

የአውሮፓ ምክር ቤት በሩሲያ ላይ ሊጣሉ ይገባል ብሎ ካስቀመጣቸው የማዕቀብ ፓኬጆች ይህ ስድስተኛው ሲሆን፣ 27ቱም የኅብረቱ አባል አገሮች ተስማምተውበታል ሲል ቢቢሲ አስፍሯል፡፡

ሩሲያ 27 በመቶ ነዳጅ ዘይትና 40 በመቶ ጋዝ ለኅብረቱ አባል አገሮች የምታቀርብ ሲሆን፣ ከዚህም በዓመት 430 ቢሊዮን ዶላር ታገኛለች፡፡

የኅብረቱ አባል አገሮች እስካሁን ድረስ በሩሲያ ነዳጅ ዘይትና ጋዝ ላይ ምንም ዓይነት ማዕቀብ ተግባራዊ ባያደርጉም፣ ጀርመን ከሩሲያ ጋዝ ለማስገባት የሚያስችላትን አዲስ ቱቦ ለመዘርጋት የነበራትን ዕቅድ ትታለች፡፡

ብሪታንያ ደግሞ ከነዳጅ ፍላጎቷ ውስጥ ስምንት በመቶ ያህሉን ከሩሲያ እያስገባች ቢሆንም ይህንን በዓመቱ መጨረሻ ለማቋረጥ ቃል ገብታለች፡፡

የኅብረቱ አባል አገሮች ከዚህ ውሳኔ መድረሳቸው እንደተሰማ፣ በአውሮፓ የነዳጅ ዘይት ዋጋ አሻቅቧል፡፡ በተለይ ካለፈው መጋቢት ወዲህ ከፍተኛ የተባለውን ዋጋ አስመዝግቧል፡፡ የበርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት ዋጋም 123 ዶላር ደርሷል፡፡

የማዕቀቡ ፓኬጅ ምንድነው?

ሩሲያ ዩክሬንን ለመውረር የጀርባ አጥንት የሆናት ከነዳጅ ሽያጭ በምታገኘው ገንዘብ ነው ብለው በተደጋጋሚ ሲገልጹ የሚሰሙት የአውሮፓ ኅብረት አባል አገሮች፣ በዓመቱ መጨረሻ ላይ ከሩሲያ በባህር የሚያስገቡት ነዳጅ ዘይት ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ተግባራዊ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህ ግን በቱቦ የሚሄደውን አይጨምርም፡፡

ፖላንድና ጀርመን ከሩሲያ ወደ አገራቸው በቱቦ የሚያስገቡትን የነዳጅ ዘይት የሚያቆሙ መሆኑን መግለጻቸው ሌላኛው የፓኬጁ ገጽታ ነው፡፡ የሩሲያ ትልቁ ሰብር ባንክ ከስዊፍት የክፍያ ሥርዓት የሚገታ መሆኑና ሦስት ተጨማሪ የሩሲያ መንግሥት የብሮድካስት ጣቢያዎች ማዕቀብ የሚጣልባቸው መሆኑም ተካቷል፡፡ ሩሲያ በዩክሬን በምታደርገው ጦርነት በጦር ወንጀል ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ ገደብ መጣልም የዚሁ ፓኬጅ አካል ነው፡፡

ማዕቀቡ በባህር የሚላክ ነዳጅ ላይ ብቻ ለምን ሆነ?

የኅብረቱ አባል አገሮች ከአንድ ሰዓት በላይ በተከራከሩበትና ልዩነታቸውን ለማጥበብ በሞከሩበት ውይይት ከሩሲያ ወደ ኅብረቱ በቱቦ የሚገባ ነዳጅ ዘይት ላይ ማዕቀብ ያልተጣው በሃንጋሪ ምክንያት ነው፡፡

ሃንጋሪ 65 በመቶ ነዳጅ ዘይት ከሩሲያ የምታስገባ ሲሆን፣ የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር አርባንም ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው፡፡ ከዚህ ባለፈ ደግሞ የባህር በር የሌላቸው ሃንጋሪ፣ ስሎቫኪያና ቼክ ሪፐብሊክ ይበልጥኑ ተጎጂ ይሆናሉ፡፡

የኅብረቱ ከፍተኛ ባለሥልጣን እንደሚሉትም፣ የባህር ወደብ የሌላቸው ሦስቱ አገሮች ተጨማሪ ዋስትና የሚሰጣቸው ሲሆን፣ የቱቦ ነዳጅ ማስተላለፊያ ችግር በሚገጥመው ጊዜ ከባህር እንዲጠቀሙ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ከሩሲያ ወደ ኅብረቱ በሚገባ ነዳጅ ዘይት ላይ ማዕቀብ መጣል፣ የአባል አገሮቹን  ፍፁም መግባት የሚሻ ሲሆን፣ ይህ ግን አሁን ላይ ምሉዕ አልሆነም፡፡ ዛሬም ማዕቀቡ ተግባራዊ ሳይደረግ ሥጋት ውስጥ የወደቁ አገሮች አሉ፡፡ ክርክርና አለመግባባት እንዳለም ተዘግቧል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ፣ በኅብረቱ ስብሰባ ላይ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት አውሮፓውያን የውስጥ ልዩነታቸውን እንዲያጠፉ ጠይቀዋል፡፡ የአውሮፓውያኑ መከፋፈል ሩሲያን ጠቅሟልም ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...