Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየጂኦስፓሺያል መረጃ የሚመሩ ግብረ ኃይሎችን ማቋቋም አልተቻለም

የጂኦስፓሺያል መረጃ የሚመሩ ግብረ ኃይሎችን ማቋቋም አልተቻለም

ቀን:

የጂኦስፓሺያል መረጃን የሚመሩ ግብረ ኃይሎችን ማቋቋም ባለመቻሉ፣ የድርጊት መርሐ ግብሩ ወደ ተግባር አለመግባቱን የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሺያል ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን የጂኦስፓሺያል መረጃ ማዕቀፍን መሠረት በማድረግ አገር አቀፍ የተቀናጀ የመረጃ አያያዝ ማዕቀፍና የድርጊት መርሐ ግብር መዘጋጀቱን፣ በስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሽያል ኢንስቲትዩት የብሔራዊ ዳታ መሠረተ ልማት ኃላፊ አቶ በሪሁ ዓለማየሁ ገልጸዋል።

በዚህም ማዕቀፍ መሠረት መረጃው ከተዘጋጀ በኋላ አጠቃቀሙን በተመለከተ ሕጋዊ ማዕቀፍ እንደሚያስፈልገው፣ ይህንኑ ለማስተዳደርና ለመቆጣጠር ግብረ ኃይሎች መቋቋም አለባቸው ብለዋል።

አገራዊ የድርጊት መርሐ ግብሩን ወደ ሥራ ለማስገባት ከሚያስፈልጉት መካከል የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ዋነኛው ሲሆን፣ ይህንን ለማድረግም በአጠቃላይ ከሚቋቋሙት ዘጠኝ ግብረ ኃይሎች መካከል አንደኛው እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

መረጃዎቹ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ ጥቅም ላይ የሚውሉ መሆናቸውን፣ ከታለመላቸው ዓላማ ውጪ ጥቅም ላይ እንዳይውሉና ለአደጋ እንዳያጋልጡ ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ያስፈልጋል ብለዋል።

በአገራዊ የጂኦስፓሺያል መረጃ ማዕቀፍ ውስጥ ተገልጋዮች፣ በተለይም የመንግሥት ተቋማት ራሳቸው እንዲቆጣጠሩ መደረጉን አቶ በሪሁ አክለዋል። ነገር ግን አጠቃቀሙን በተመለከተ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ቁጥጥር ያስፈልገዋል ብለዋል።

በአገር ደረጃ የጂኦስፓሺያል መረጃ አጠቃቀሙ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑን፣ በተሻለ ደረጃ ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘው በደኅንነት ዘርፉ ነው ያሉት ኃላፊው ነገር ግን በሁሉም ዘርፎች ላይ ከፍተኛ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም በመንገድ፣ በቱሪዝም፣ በመሬት አስተዳደርና በመሬት ላይ ለሚሠሩ ሥራዎች አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በግብርና ዘርፍም በማዳበሪያ አጠቃቀም፣ በውኃ ሥርጭት፣ እንዲሁም በሰብል በሽታ መረጃዎችን ሰብስቦ ጥቅም ላይ ለማዋል የጂኦስፓሺያል መረጃ ሥርዓት አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል።

እነዚህ ሁሉ መረጃዎች ጥቅም ላይ ሲውሉ ደረጃቸውን በጠበቀ መንገድ እንዲሆንና ለአደጋ እንዳያጋልጡ፣ የሚዘጋጀው የሕግ ማዕቀፍ ጠቃሚ እንደሚሆን አቶ በሪሁ አክለዋል። ይህም የተዘጋጀውን አገራዊ የድርጊት መርሐ ግብር ወደ ተግባር ለማስገባትና የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት ለመወሰን ያግዛል ብለዋል።

ነገር ግን በ2014 በጀት ዓመት የድርጊት መርሐ ግብሩ ወደ ሥራ እንዲገባ ቢታቀድም የሕግ ማዕቀፉ ባለመኖሩና ለዚህም አስፈላጊ የሆነው ግብረ ኃይል ባለመቋቋሙ ወደ ሥራ መግባት አልቻለም ብለዋል።

ለዚህም የተቋማት አደረጃጀት በየጊዜው መለዋወጥ ግብረ ኃይሉን ለማቋቋም አስቸጋሪ እንዳደረገው ገልጸዋል። በዚህም ምክንያት የሕግ ማዕቀፉ ዝግጅት እስከ 2015 በጀት ዓመት ሩብ ዓመት ሊዘገይ እንደሚችል አክለዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...