Wednesday, September 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአፍሪካ ሕፃናት የጎጂ ልማዶች ሰለባ መሆናቸውንና ትኩረት እንዳልተሰጣቸው ተገለጸ

የአፍሪካ ሕፃናት የጎጂ ልማዶች ሰለባ መሆናቸውንና ትኩረት እንዳልተሰጣቸው ተገለጸ

ቀን:

በአፍሪካ ሕፃናት ከጎጂ መንፈሳዊ ልማዶች ጋር ተያይዞ ለስቃይ፣ በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለአካላዊና ለሥነ ልቦናዊ ጥቃቶች መጋለጣቸውንና መንግሥታቱም እያዩ እንዳላዩ መሆናቸውን አፍሪካ ቻይልድ ፖሊስ ፎረም አስታወቀ።

ሕፃናቱ ከጥንቆላና ከጎጂ መንፈሳዊ ልማዶች ጋር በተያያዘ እየደረሰባቸው ያለውን ስቃይ እንዲያበቃ፣ የአፍሪካ መንግሥታት በሚጠበቅባቸው ልክ እንዲሠሩ ግንቦት 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በስካይ ላይት ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተጠይቀዋል።

የአፍሪካ ቻይልድ ፖሊሲ ፎረም በጥናቱ እንደጠቆመው፣ ሕፃናቱ በጠንቋይነት የሚወነጅሉና በጎጂ መንፈሳዊ ልማዶች ሰለባ እንደሚሆኑ፣ አገሮቹ ድርጊቶቹን ለመከላከል ስምምነት ቢያደርጉም ተግባሩ ላይ የሉበትም ይላል።

በጥንቆላ ተግባር የሚከሰሱ ሕፃናት፣ የሚደርሰው ስቃይ፣ በጥንቆላ ሰበብ  መገደል፣ ለግዳጅ ኑዛዜ፣ ለድብደባና እንግልት እንደሚዳረጉ ጥናቱ ያመላክታል።

በባህላዊ ልማድ መሠረት ‹‹የሚያነፃ›› ተብለው በማኅበረሰብ የሚታመኑ ባህላዊ መድኃኒቶች ማስዋጥ፣ ከቤት ማሳደድ፣ ማግለልና ከፍ ሲልም የግድያ ዕርምጃ   እንደሚወሰድባቸው ይጠቁማል።

የአፍሪካ ቻይልድ ፖሊሲ ፎረም ዋና ዳይሬክተር ጁዋን ንያኑኪ እንደተናገሩት፣ ከጥንቆላ ጋር በተያያዘ በልጆች ላይ የሚቀርበው ክስና ጎጂ መንፈሳዊ ጥቃት፣ በአፍሪካውያን እምነት፣ ባህልና ልምድ ውስጥ በጥልቀት ተቀብሮ የሚገኝ እውነታና በሚስጥር የተያዘ ጉዳይ ነው።

በጥናቱ እንደተቀመጠው ችግሩን ለመፍታት ከላይ የተጠቀሱትን ከፍተኛ ወንጀሎች መሆናቸው ታውቆ ሕጋዊ ቅጣት ሊጣልባቸው እንደሚገባ ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡  

ጥናቱ የተደረገባቸው በአፍሪካ አምስት አገሮች ሲሆን፣ መረጃው አይሰብሰብ እንጂ በሌሎች አገሮችም እንዳሉ የሚያሳዩ ሁኔታዎች መኖራቸው ተገልጿል፡፡

በተለይም በአልቤኒዝም ጋር የተወለዱ ልጆችን በመጥለፍ የሰውነት ክፍሎቻቸውን ለመድኃኒትነት ሲባል መውሰድና ከፍ ሲልም ግድያን እንደሚካሄድባቸው በጥናቱ ተቀምጧል፡፡

ዋና ዳይሬክተሯ እንደተናገሩት፣ ሕፃናቱን የማግለል፣ ችላ የመባልና የአድሎ ስሜት ጠባሳ በአዕምሮቸው ተቀርፆ ሙሉ ሕይወታቸውን በዚህ ክስተት እንዲኖሩ ይዳረጋሉ፡፡  

ሪፖርቱ የአፍሪካ አገሮች ከጥንቆላ ጋር በተያያዘ በሕፃናት ላይ የሚቀርበው ክስና ጎጂ መንፈሳዊ ጥቃት በቂ የሰውና የፋይናንስ ግብዓት እንደሌላቸው የገለጹት ዳይሬክተሯ፣ ዓለም አቀፍ ለጋሾች እጅግ ውስን የሆነ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

የወንጀል ድርጊቶቹ በመላው አኅጉራት ውስጥ እጅግ በድብቅ ከሆኑና ሥር ከሰደዱ ጎጂ ልማዳዊ ተግባራት ውስጥ ለመንግሥታቱ አዳጋች ከሆኑት ውስጥ ዋነኞቹ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የአፍሪካን ቻይልድ ፖሊሲ ፎረም የሕፃናት ዕድገትና ጥበቃ ፕሮግራም (Child Development and Protect Program) ኃላፊ አቶ ረታ ጌታቸው እንደተናገሩት፣ ከጎጂና ጥንቆላ ጋር የተያያዙ እምነቶች በሕፃናት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመቅረፍ የሚያግዝ ጥናት ነው፡፡

ጥናቱ በሕፃናት ላይ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚደርስባቸውን ጉዳት ለመከላከል የሚያግዝ መሆኑን፣ የአፍሪካ መንግሥታትና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በጉዳዩ ላይ ትኩረት አልሰጡትም ተብሏል፡፡

ማላዊ፣ ታንዛኒያ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎና ሞሮኮ ላይ ትኩረት ያደረገ ጥናት መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ በሌሎች የአፍሪካ አገሮችም ችግሮች  እንዳሉ ገልጸዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችና ሌሎችም ተቋማት በዚህ ጉዳይ ትኩረት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

ከጥናቱ መረዳት እንደሚቻለው ተጎጂ ሕፃናት ውስጥ በአብዛኛው ሴቶች መሆናቸውን፣ አካል ጉዳተኞች፣ መንታ ልጆችና አልቢኒዝ ለችግሩ የተጋለጡ ናቸው ተብሏል፡፡

የአፍሪካ ሕፃናት መብትና ደኅንነት ስምምነትና ዓለም አቀፍን የሕፃናት መብት ኮንቬንሽን ቢፀድቅም፣ ተግባሩ ላይ አገሮቹ እንደሌሉበት ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...