Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናሁከትና ብጥብጥ አስነስተዋል በሚል ተጠርጥረው በታሰሩ ጋዜጠኞች  ላይ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ

ሁከትና ብጥብጥ አስነስተዋል በሚል ተጠርጥረው በታሰሩ ጋዜጠኞች  ላይ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ

ቀን:

የፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ ጋዜጠኛ ከእስር ተለቃለች

ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ በፀጥታ ኃይሎች የታሰረችው የሮሃ ሚዲያ ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድና የፍትሕ መጽሔት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ትናንት ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ፡፡

ጋዜጠኛ መዓዛ ፍርድ ቤት የቀረበችው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን፣ ፖሊስ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ ማስነሳት›› በሚል መጠርጠሯን ለፍርድ ቤቱ አስታውቆ፣ በጉዳዩ ላይም መረጃ ለማሰባሰብ የ14 ቀን ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡

ጋዜጠኛዋ ሠራች የተባለው ወንጀል ተፈጽሞ ቢሆን እንኳን፣ ጉዳዩ ሊታይ የሚገባው በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ መሆኑን ጠበቆቿ ለፍርድ ቤቱ አስረድተው፣ በእስር እንድትቆይ የሕግ መሠረት እንደሌለ በማስረዳት ተከራክረዋል። አክለውም ጋዜጠኛዋ ከወራት በፊት ታስራ ማስረጃ ሊቀርብባት ባለመቻሉ በነፃ መለቀቋን አስታውሰው፣ አሁንም ሞጋች ጋዜጠኛ መሆኗ እንጂ የሠራችው ወንጀል እንደሌለና ይኼንን ፍርድ ቤቱ ሊመለከተው እንደሚገባ ሞግተዋል። ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ሰባት ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል፡፡

ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ውሎ በማግስቱ ግንቦት 19 ቀን ፍርድ ቤት ቀርቦ የተጠረጠረበት ወንጀል መታየት ያለበት በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ነው አይደለም በሚለው ላይ ብይን ለመስጠት ለግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም. ተቀጥሮ ፍርድ ቤት የቀረበው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝም ላይ የአሥር ቀናት የምርመራ ጊዜ ተፈቅዷ። የምርመራ ጊዜውን የፈቀደው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ሲሆን፣ የምርምራ ጊዜውን የፈቀደው የተከሳሽ ጠበቃ ያቀረቡትን መከራከሪያና የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ነው። በመሆኑም ለግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል።

ሌላው ዓርብ ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር የዋለው ‹‹አልፋ ቴሌቪዥን››  ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ሲሆን ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡ ጋዜጠኛ በቃሉ የተጠረጠረው ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት፣ ሃይማኖት ከሃይማኖት ጋር በማጋጨትና ሕዝብ በመንግሥት ላይ በማነሳሳት ወንጀል መሆኑን ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቷል፡፡ ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ ለማጣራት 14 ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቆ 12 ቀናት ተፈቅዶለታል፡፡ በመሆኑም ለሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

ሐሙስ ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ ከሥራ ቦታዋ ስትወጣ በፀጥታ ኃይሎች ታስራ የነበረችው የ‹‹ፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ›› የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ ሰቦንቱ አህመድ ስትሆን፣ ከእስር መለቀቋ ታውቋል፡፡

በ‹‹ፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ›› ቴሌቪዥን ጣቢያ ዜና አንባቢና የመዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጅ የሆነችው ሰቦንቱ፣ በታሰረች በማግስቱ ወደ ቢሾፍቱ ከተማ መወሰዷ ተገልጾ ነበር።

ለሦስት ቀናት በእስር የቆየችው ሰቦንቱ፤ ከትናንት በስቲያ ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ አራት ሰዓት ተኩል ገደማ በዋስ መለቀቋ ታውቋል፡፡ ጋዜጠኛዋን ‹‹ስንፈልግሽ ትመጫለሽ›› በሚል  የኦሮሚያ ፖሊስ ከእስር እንደፈታትም ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...