Skip to main content
x
ብሔራዊ ባንክ ገለልተኛ ሆኖ እንዲዋቀር ጥሪ ቀረበ
ብሔራዊ ባንክ ገለልተኛ ሆኖ እንዲዋቀር ጥሪ ቀረበ
በርካታ ትችቶች የሚሰነዘርበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማዕከላዊ ባንክነቱን ሚና በአግባቡ እንዲጫወት፣ ከማንኛውም የመንግሥት ተፅዕኖ ነፃ ሆኖ እንደ አዲስ እንዲዋቀር የተለያዩ ባለሙያዎች ሐሳብ ቀረቡ፡፡
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ሽኝት
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ሽኝት
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአንድ ቀን ብሔራዊ የሐዘን ቀን ያወጀላቸው የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ረቡዕ ታኅሳስ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከመፈጸሙ በፊት፣ ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጀምሮ በሚሌኒየም አዳራሽ የአስከሬን ስንብት ይደረጋል።
የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትሩ ለዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አባልነት እንዲሾሙ የቀረበውን ጥያቄ ፓርላማው ውድቅ አደረገ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አባልነት ከቀረቡለት ዕጩዎች መካከል፣ በምክር ቤቱ የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር የሆኑትን የአቶ ገብረ እግዚአብሔር አርዓያን የሹመት ጥያቄ እንደማይቀበለው በመግለጽ ውድቅ አደረገ።
የኢትዮጵያ ጦር ኃይል አቅም በአፍሪካ ስድስተኛ ደረጃ መያዙን ዓለም አቀፍ ሪፖርት አመለከተ
የኢትዮጵያ ጦር ኃይል አቅም በአፍሪካ ስድስተኛ ደረጃ መያዙን ዓለም አቀፍ ሪፖርት አመለከተ
የአገሮችን ወታደራዊ አቅም ከኢኮኖሚያዊ አቋማቸውን በመንተራስ ደረጃቸውን ይፋ የሚያደርገውና ‹‹ግሎባል ፋየርፓወር›› የተሰኘው የአሜሪካ ተቋም፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ኃያል ከሚባሉ አሥር ዋና ዋና አገሮች ውስጥ በስድስተኛ ደረጃ የሚያሠልፋት የጦር ኃይል አቅም እንዳላት ይፋ አደረገ፡፡
በሞያሌ የተቀሰቀሰው ግጭት እየተባባሰ ነው
ሰሞኑን በሞያሌ ከተማ ለዘመናት አብረው በኖሩት የኦሮሞና የሶማሌ ተወላጆች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ከመረጋጋት ይልቅ እየባሰበት መምጣቱን፣ የሁለቱም ተወላጆች ወደ አጎራባች ኬንያ መሰደድ መቀጠላቸውን ሪፖርተር ያነጋገራቸው ምንጮች ገለጹ።
በሕገወጥነት የተጠረጠሩ 28 ትልልቅ የሪል ስቴት ኩባንያዎች ታገዱ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሕገወጥነት የጠረጠራቸውን 28 ትልልቅ የሪል ስቴት ኩባንያዎች አገደ፡፡ በምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የተቋቋመው ኮሚቴ በሪል ስቴት ኩባንያዎች ላይ የዳሰሳ ጥናት ካደረገ በኋላ አገልግሎት እንዳያገኙ አግዷል፡፡
ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ለኢትዮጵያ ገቢ ንግድ ዋስትና የሚሰጥ ስምምነት ፈረመ
ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ለኢትዮጵያ ገቢ ንግድ ዋስትና የሚሰጥ ስምምነት ፈረመ
ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (አይኤፍሲ) ለኢትዮጵያ አስመጪዎች ዕፎይታ የሚሰጥ የገቢ ንግድ ዋስትና ስምምነት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ተፈራረመ፡፡ በመንግሥት በኩል ስምምነቱ የኢትዮጵያን የገቢ ንግድ ሙሉ በሙሉ የዋስትና ከለላ የሚሰጥ ዕድል መፈጠሩ ተስፋ ተደርጓል፡፡
ማስታወቂያ

ለዜና መጽሔታችን ደንበኝነት ይመዝገቡ

ዜና መጽሔት

ዓለም

ሳዑዲ አሜሪካ በአገሬ ጉዳይ ጣልቃ ገብታለች ስትል አወገዘች
ሳዑዲ አሜሪካ በአገሬ ጉዳይ ጣልቃ ገብታለች ስትል አወገዘች
የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት፣ በየመን ላይ በጥምር ለከፈተው ጦርነት የጀርባ አጥንት ሆና ስትደግፍ የነበረችው አሜሪካ ከጦርነቱ ራሴን አገላለሁ ማለቷን አወገዘ፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው፣ የአሜሪካ ሴኔት የአሜሪካ መንግሥት ሳዑዲ ዓረቢያ የምትመራውን ወታደራዊ ጥምረት መደገፍ የለበትም በሚል ሰሞኑን ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ ሳዑዲ ከወዳጇ አሜሪካ ጋር የቃላት ጦርነት ገብታለች፡፡
ፈረንሣይን የፈተነው ‹‹የሎው ቬስት›› ተቃውሞ
ፈረንሣይን የፈተነው ‹‹የሎው ቬስት›› ተቃውሞ
ፈረንሣውያን በነዳጅ ዘይት ላይ የተደረገውን የግብር ጭማሪና የኑሮውን ውድነት በመቃወም ለአራት ተከታታይ ሰንበቶች በዋና ከተማዋ ፓሪስና በተለያዩ ከተሞቿ ‹‹የሎው ቬስት›› (አንፀባራቂ ጃኬት) በመልበስ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡
ጆርጅ ኸርበርት ዎከር ቡሽ (1924-2018)
ጆርጅ ኸርበርት ዎከር ቡሽ (1924-2018)
በአሜሪካ ማሳቹሰትስ እ.ኤ.አ. ሰኔ 12 ቀን 1924 የተወለዱትና የአሜሪካ 41ኛ ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገሉት ጆርጅ ኸርበርት ዎከር ቡሽ (ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ትልቁ) ዜና ዕረፍታቸው የተሰማው ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡
በአሜሪካና ብሪታኒያ ንግድ ላይ ያጠላው የብሪግዚት ውል
በአሜሪካና ብሪታኒያ ንግድ ላይ ያጠላው የብሪግዚት ውል
ብዙዎች የፖለቲካ ብስለት የላቸውም ሲሉ የሚተቿቸው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ‹‹አሜሪካ ፈርስት›› [አሜሪካ ትቅደም] በሚል መፈክራቸው ይታወቃሉ፡፡
አቅጣጫውን እየቀየረ ያለው የዓለም አመራር
አቅጣጫውን እየቀየረ ያለው የዓለም አመራር
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው አስቀድሞ ለረዥም ዓመታት ሲያራምዱት ከነበረው ‹‹ቅድሚያ ለአሜሪካ›› ከሚለው አቋማቸው ጋር በእኩል ሲያራምዱት የነበረው፣ አሜሪካ የዓለም ፖሊስነትን ማቆም አለባት የሚለው አቋማቸው ነው፡፡
በእንቆቅልሽ የተሞላው የዶናልድ ትራምፕና የኪም ጆንግ ኡን የሲንጋፖር ውይይትና ስምምነት
በእንቆቅልሽ የተሞላው የዶናልድ ትራምፕና የኪም ጆንግ ኡን የሲንጋፖር ውይይትና ስምምነት
ሀዋርድ ኤክስ የሚኖረው ሆንግ ኮንግ ሲሆን ቁርጥ የሰሜን ኮሪያን ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡንን ይመስላል፡፡ ከዚህ ቀደም በድርጊት ማስመሰል ጥበቡ ዶናልድ ትራምፕን ከሚያስመስለው የሙያ አጋሩ ዴኒስ አለን ጋር በመሆን፣ በደቡብ ኮሪያ ፕዮንግቻንግ በተካሄደው የክረምት ኦሊምፒክ በጭራሽ ካልገመቱ ተሳታፊዎች ጋር ፎቶ በመነሳትና አብሮ በመቀመጥ ከፍተኛ ትኩረትን ሊስብ የቻለ ኮሜዲያን ነው፡፡
ማስታወቂያ
የተመረጡ

ምን እየሰሩ ነው?

‹‹ፍላጎቴ አርሶ አደሩ ጥሩ ገበያ እንዲያገኝና ምርቱ ጥራት እንዳለው እንዲመሰከርለት ነው››
‹‹ፍላጎቴ አርሶ አደሩ ጥሩ ገበያ እንዲያገኝና ምርቱ ጥራት እንዳለው እንዲመሰከርለት ነው››
አቶ በለጠ በየነ የብሌስ አግሪ ፉድ ላቦራቶሪ ሰርቪስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር መሥራችና የቦርድ ሊቀመንበር ናቸው፡፡ በ1969 ዓ.ም. ፋፋ የምግብ ድርጅት ሲመሠረት ጀምሮ በተመጣጠነ ምግብ ማቀነባበር ዙሪያ ተሳትፈዋል፡፡ ከ1985 ዓ.ም. ወዲህ በዚሁ ዘርፍ የግል ድርጅት በመክፈት እየሠሩ ይገኛሉ፡፡
‹‹በዕርዳታና በበጀት ብቻ የንፁህ ውኃ አቅርቦትና የመፀዳጃ ቤት ችግር አይፈታም›› አቶ ሰልፊሶ ኪታቦ፣ በኢትዮጵያ የወተር ኦርግ ዳይሬክተር
‹‹በዕርዳታና በበጀት ብቻ የንፁህ ውኃ አቅርቦትና የመፀዳጃ ቤት ችግር አይፈታም›› አቶ ሰልፊሶ ኪታቦ፣ በኢትዮጵያ የወተር ኦርግ ዳይሬክተር
አቶ ሰልፊሶ ኪታቦ በኢትዮጵያ የወተር ኦርግ  ዳይሬክተር ናቸው፡፡ ወተር ኦርግ ከተቋቋመ 25 ዓመታትን ያስቆረጠ ሲሆን፣ በ13 አገሮች ቅርንጫፎቹን ከፍቶ በንፁህ ውኃና መፀዳጃ ቤት ተደራሽነት ላይ እየሠራ ይገኛል፡፡
‹የትራፊክ አደጋን ለመቆጣጠር ከጊዜ መለዋወጥ ጋር የሚሄዱ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀምን እንመክራለን››
‹የትራፊክ አደጋን ለመቆጣጠር ከጊዜ መለዋወጥ ጋር የሚሄዱ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀምን እንመክራለን››
ስዊድን ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በጋራ ከምትሠራባቸው መስኮች አንዱ የትራንስፖርት ዘርፍ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የትራንስፖርት ዘርፍ አለመሳለጥ ተጠቃሚውን ከማጉላላቱም በላይ የብዙዎችን ሕይወት የሚቀጥፍ የትራፊክ አደጋ በየዓመቱ ለመመዝገቡ ምክንያት ነው፡፡
‹‹በግድ መምህር ሁን ብለን የምንለፋው ወደ ሌላ ትምህርት ዘርፍ መግባት ያልቻለውን ነው››
‹‹በግድ መምህር ሁን ብለን የምንለፋው ወደ ሌላ ትምህርት ዘርፍ መግባት ያልቻለውን ነው››
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ሬጉላቶሪ ኤጀንሲ በ2010 ዓ.ም. በግልና በመንግሥት ትምህርት ተቋማት ያደረገውን የኢንስፔክሽን ሥራ ከሳምንት በፊት ይፋ ባደረገበት ወቅት በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የተጠኑ ጥናቶች ውጤትም ተገልጸው ነበር፡፡
አባጣ ጎርባጣ የበዛበት የኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን የንግድ ድርጅት የመቀላቀል ጉዞ
አባጣ ጎርባጣ የበዛበት የኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን የንግድ ድርጅት የመቀላቀል ጉዞ
ከሳምንታት በፊት በአገሮች የንግድ ሥርዓት ፈተናዎች ላይ ምሥራቅ አፍሪካ ያለውን ምልከታ አስመልክቶ በኬንያ ናይሮቢ ሴሚናር ተካሂዶ ነበር፡፡ በወቅቱ በዓለም አቀፉ የንግድ ድርጅት ዙሪያ ያሉ ፈተናዎች፣ በድርጅቱ አባል አገሮች መካከል የንግድ ጦርነት እያንሰራራ መምጣቱና ንግድን በአካባቢ መወሰን የተነሱ ጉዳዮች ነበሩ፡፡
የኦሮሚያ ልማት ማኅበር የብር ኢዮቤልዩ አበርክቶ
የኦሮሚያ ልማት ማኅበር የብር ኢዮቤልዩ አበርክቶ
የኦሮሚያ ልማት ማኅበር (ኦልማ) በ1986 ዓ.ም. ሲቋቋም ክልሉ እንደ ሌሎች ክልሎች መሠረተ ልማት ያልተስፋፋበትና ያሉትም መሠረተ ልማቶች ቢሆኑ በከተማ አካባቢ የተወሰኑበት ነበር፡፡ መንግሥት አካባቢውን ለማልማት ከሚሠራው በተጨማሪ ኦልማ ክፍተቶችንና ጉድለቶችን ለመሙላት እየሠራ ይገኛል፡፡