Skip to main content
x
አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ተያዙ
አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ተያዙ
የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ በረከት ስምኦንና የጥረት ኮርፖሬት ዋና አስፈጻሚና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ)፣ ዛሬ ጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡
የመከላከያ ቀን በአዳማ ከተማ ይከበራል
የመከላከያ ቀን በአዳማ ከተማ ይከበራል
ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ የሚከበረው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቀን በአየር ኃይልና በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ትብብር በአዳማ ከተማ እንደሚከበር፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አስታወቀ፡፡ በዓሉም የካቲት 7 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚከበር ተገልጿል፡፡
ኦዴፓና ኦነግ በመሀላቸው የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት ተስማሙ
ኦዴፓና ኦነግ በመሀላቸው የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት ተስማሙ
በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ለወራት ሲወዛገቡ የቆዩት የክልሉ ገዥ ፓርቲ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦዴፓ) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ አባ ገዳዎች ኅብረት ባዘጋጀው የዕርቀ ሰላም ውይይት ላይ ችግሮቻቸውን ለመፍታት ከስምምነት ደረሱ፡፡
ቤቶች ኮርፖሬሽን ያደረገው የንግድ ቤቶች ኪራይ ጭማሪ በድጋሚ እንዲታይ ተከራዮች ጠየቁ
ቤቶች ኮርፖሬሽን ያደረገው የንግድ ቤቶች ኪራይ ጭማሪ በድጋሚ እንዲታይ ተከራዮች ጠየቁ
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ በሚያስተዳድራቸው የንግድ ቤቶች ኪራይ ዋጋ ላይ በቅርቡ ያደረገው ጭማሪ የተጋነነ በመሆኑ በድጋሚ እንዲጠና ተከራዮች ጠየቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ የኢትዮጵያን የለውጥ ጉዞና መፃኢ ዕድሎች ለዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ታዳሚዎች ያስረዳሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ የኢትዮጵያን የለውጥ ጉዞና መፃኢ ዕድሎች ለዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ታዳሚዎች ያስረዳሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የበርካታ አገሮች መሪዎችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ባለሀብቶችና የዓለም አቀፍ ተቋማት አመራሮች በሚታደሙበት የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም (መድረክ) ተገኝተው፣ በእሳቸው አመራር በኢትዮጵያ ስለተጀመረው የለውጥ ጉዞና መፃኢ ዕድሎች ረቡዕ ጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ከቀትር በኃላ ያስረዳሉ።
ኮሪያ ሆስፒታል በሕፃን ልጅ ላይ ከባድ የሕክምና ስህተት በመፈጸም የ23.6 ሚሊዮን ብር ክስ ቀረበበት
የሽንት ቧንቧ ችግር (Hypospedia) ሕክምና ለማግኘት ገብቶ ቀዶ ሕክምና ከተደረገለት በኋላ፣ ሕክምና በተደረገበት ጠረጴዛ ላይ እያለ ወደ ሳንባው የተላከ መተንፈሻን ቱቦ በመንቀል ሕፃኑ ሙሉ ለሙሉ ፓራላይዝድ (መንቀሳቀስ እንዳይችል) አድርጓል የተባለው የኮሪያ አጠቃላይ ሆስፒታል፣ የ23.6 ሚሊዮን ብር የፍትሐ ብሔር ክስ ተመሠረተበት፡፡
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ መድኃኒቶችና የሕክምና መሣሪያዎች ግዥ በመፈጸም ላይ ነኝ አለ
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ መድኃኒቶችና የሕክምና መሣሪያዎች ግዥ በመፈጸም ላይ ነኝ አለ
በአገሪቱ የሚስተዋለውን የመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያዎች እጥረት በተወሰነ ደረጃ ለመቅረፍ፣ 6.4 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ግዥ በመፈጸም ሒደት ላይ መሆኑን የጤና ሚኒስትሩ አሚር አማን (ዶ/ር) ገለጹ።
ማስታወቂያ

ለዜና መጽሔታችን ደንበኝነት ይመዝገቡ

ዜና መጽሔት
ማስታወቂያ
ማስታወቂያ

ዓለም

እስራኤልና ኢራን በምድረ ሶሪያ
እስራኤልና ኢራን በምድረ ሶሪያ
አሜሪካና ሩሲያ ጎራ ለይተው የእጅ አዙር ጦርነታቸውን የሚያካሂዱባት ሶሪያ ከትናንት በስቲያ (ጥር 12 ቀን 2011 ዓ.ም.)  የእስራኤልን ሚሳይሎች ስታስተናግድ አድራለች፡፡
በዚምባቡዌ ተቃውሞ ያስከተለው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ
በዚምባቡዌ ተቃውሞ ያስከተለው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ
ዚምባቤያውያን የቤንዚንና ናፍጣ ዋጋ መጨመርን ተከትሎ በዚምባቡዌ ዋና ከተማ ሃራሬና በቡላዋዮ ለተቃውሞ ወጥተዋል፡፡ መንግሥት በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጉን ካሳወቀ በኋላ ለተቃውሞ የወጡት ዚምባቤያውያን በየመንገዱ ጎማ ሲያቃጥሉና ድንጋይ ሲወረውሩ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ተስተውለዋል፡፡
የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆን ኡንግ የቻይና ጉብኝት
የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆን ኡንግ የቻይና ጉብኝት
የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆን ኡንግ ለአራት ቀናት ጉብኝት ቻይና ገብተዋል፡፡ ከአሜሪካ ጋር ለሁለተኛ ጊዜ ለመገናኘት ዝግጅት እየተደረገ ባለበት ወቅት ፕሬዚዳንት ኪም ቻይና የገቡት፣ በቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂፒንግ ግብዣ እንደሆነ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
የአሜሪካ ጦር ከሶርያ መውጣት
የአሜሪካ ጦር ከሶርያ መውጣት
አሜሪካ በሶርያ ያሏትን ወታደሮች በሙሉ እንደምታስወጣ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተናገሩት ከሁለት ሳምንታት በፊት ነበር፡፡ ‹‹ሁሉም ወደ አገራቸው ይመለሳሉ፡፡ አሁን ይመለሳሉ፤›› ብለው ፕሬዚዳንቱ ሲናገሩ፣ የአገሪቱ ባለሥልጣናትም የአሜሪካ ወታደሮች ሶርያን በ30 ቀናት ውስጥ እንዲለቁ ጊዜ መሰጠቱን አሳውቀው ነበር፡፡
በተጠናቀቀው 2018 ትኩረት ያገኙ ዘገባዎች
በተጠናቀቀው 2018 ትኩረት ያገኙ ዘገባዎች
የፈረንጆቹ ዓመተ 2018 አመፆች፣ ጦርነቶች፣ ስምምነቶች፣ አደጋዎችና ሌሎችንም ክስተቶች አስተናግዷል፡፡ ዓመቱ ለማብቃት የሳምንት ያህል ዕድሜ ሲቀረው፣ በዓመቱ በዓለም መነጋገሪያ የተባሉ ክንውኖች በየመገናኛ ብዙኃኑ ተዘግበዋል፡፡ የተለያዩ መገናኛ ብዙኃንና ብሎገሮች እንደራሳቸው ዕይታ ዋና ነበሩ ያሏቸውን አትተዋል፡፡
ሳዑዲ አሜሪካ በአገሬ ጉዳይ ጣልቃ ገብታለች ስትል አወገዘች
ሳዑዲ አሜሪካ በአገሬ ጉዳይ ጣልቃ ገብታለች ስትል አወገዘች
የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት፣ በየመን ላይ በጥምር ለከፈተው ጦርነት የጀርባ አጥንት ሆና ስትደግፍ የነበረችው አሜሪካ ከጦርነቱ ራሴን አገላለሁ ማለቷን አወገዘ፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው፣ የአሜሪካ ሴኔት የአሜሪካ መንግሥት ሳዑዲ ዓረቢያ የምትመራውን ወታደራዊ ጥምረት መደገፍ የለበትም በሚል ሰሞኑን ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ ሳዑዲ ከወዳጇ አሜሪካ ጋር የቃላት ጦርነት ገብታለች፡፡

ምን እየሰሩ ነው?

‹‹የተማሪዎች ምገባ በመንግሥት በጀት መካተቱ ትልቅ ስኬት ነው›› ወይዘሪት ሜቲ ታምራት፣ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የሕፃናት ጤናና ምግብ ባለሙያ
‹‹የተማሪዎች ምገባ በመንግሥት በጀት መካተቱ ትልቅ ስኬት ነው›› ወይዘሪት ሜቲ ታምራት፣ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የሕፃናት ጤናና ምግብ ባለሙያ
በአስከፊ ድህነት ውስጥ ከሚገኙ የዓለም አገሮች ተርታ በግንባር ቀደምነት የምትታወቀው ኢትዮጵያ ብዙ አሰቃቂ የድህነት ታሪኮችም የሚሰማባት ምድር ነች፡፡ የዜጎችን መሠረታዊ ፍላጎት ማሟላት አሁንም ድረስ አንገብጋቢ ጥያቄ ነው፡፡ የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት የማይታሰብ ሆኖ 40 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ የቀነጨረ ነው ይባላል፡፡ በዚህ ማኅበራዊ ችግር ሕፃናት ዋነኛ ገፈት ቀማሽ ናቸው፡፡
‹‹አሽከርካሪዎች የመጀመርያ ሕክምና ዕርዳታ አሰጣጥን ቢሠለጥኑ የሞት አደጋን መቀነስ ይቻላል›› አቶ ተስፋዬ ንጉሤ፣ የአዲስ አበባ አሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ ተቋማት ማኅበር ፕሬዚዳንት
‹‹አሽከርካሪዎች የመጀመርያ ሕክምና ዕርዳታ አሰጣጥን ቢሠለጥኑ የሞት አደጋን መቀነስ ይቻላል›› አቶ ተስፋዬ ንጉሤ፣ የአዲስ አበባ አሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ ተቋማት ማኅበር ፕሬዚዳንት
አዲስ አበባ ውስጥ 78 የመንግሥትና የግል አሽከርካሪ ማሠልጠኛ ተቋማት ይገኛሉ፡፡ ሕጋዊ ፈቃድ አግኝተው ከሚንቀሳቀሱት ተቋማት መካከል 62ቱ በአዲስ አበባ አሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ ተቋማት ማኅበር ታቅፈዋል፡፡
ከእኩዮቻቸው ወደኋላ የቀሩ ሕፃናትን የመርዳት ጅማሮ
ከእኩዮቻቸው ወደኋላ የቀሩ ሕፃናትን የመርዳት ጅማሮ
ወጣት እመቤት አይቸው የሙዚቃ ትምህርቷን የተከታተለችው በተፈሪ መኮንን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ነው፡፡ በ2010 ዓ.ም. የሦስት ዓመት ትምህርቷን አጠናቃ በአድቫንስድ ዲፕሎማ በኪቦርድ ከተመረቀች በኋላ ትኩረቷን ያደረገችው የትምህርት አቀባበል ችግር፣ የአዕምሮ ውስንነት ወይም ከሌሎች እኩያ ተማሪዎች ጋር በመግባባትና ትምህርት በመቀበል ቀረት የሚሉ ልጆችን ሙዚቃ ትምህርት ብናስተምራቸው ትኩረት የመስጠት ችሎታቸው ይዳብራል፣ ትምህርታቸውም ይቃናል በሚለው ላይ ነው፡፡
‹‹አካሄዱን አልተከተላችሁም ተብለን ፋብሪካ ለመገንባት የገዛነውን ማሽን ለማስቀመጥ ተገደናል›› አቶ ሲራክ ከተማ፣ የኔግራ ዘይት ፋብሪካ ባለቤት
‹‹አካሄዱን አልተከተላችሁም ተብለን ፋብሪካ ለመገንባት የገዛነውን ማሽን ለማስቀመጥ ተገደናል›› አቶ ሲራክ ከተማ፣ የኔግራ ዘይት ፋብሪካ ባለቤት
አቶ ሲራክ ከተማ ይባላሉ፡፡ ተወልደው ያደጉት በአዲስ አበባ ከተማ ካዛንቺስ አካባቢ ነው፡፡ የመጀመርያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በናዝሬት መጽሐፍ ቅዱስ አካዴሚ እስከ 11ኛ ክፍል ተምረዋል፡፡ የ11ኛ ክፍል ተማሪ እያሉ ደርግ የንጉሡን አገዛዝ በኃይል በመገልበጥ ሥልጣን ላይ የወጣበት ዘመን ነበር፡፡
‹‹በዚህ ዓመት ብቻ እስከ 80 ሚሊዮን ብር የሚገመት የላቦራቶሪ ዕቃዎች እያሟላን ነው›› አቶ ኮራ ጦሹኔ የጂማ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት
‹‹በዚህ ዓመት ብቻ እስከ 80 ሚሊዮን ብር የሚገመት የላቦራቶሪ ዕቃዎች እያሟላን ነው›› አቶ ኮራ ጦሹኔ የጂማ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት
ጂማ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ቀደምት ከሚባሉት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ነው፡፡ መሠረታዊ የመማሪያ መሠረተ ልማቶችን ማስፋፋት ላይ ትኩረቱን አድርጎ ይሠራ የነበረው ዩኒቨርሲቲው የመማሪያ ክፍሎች፣ የላቦራቶሪና ወርክሾፕ እንዲሁም የተማሪዎች ማደሪያ ሕንፃዎች ግንባታ ላይ በስፋት ሲሠራ ቆይቷል፡፡
‹‹ፍላጎቴ አርሶ አደሩ ጥሩ ገበያ እንዲያገኝና ምርቱ ጥራት እንዳለው እንዲመሰከርለት ነው››
‹‹ፍላጎቴ አርሶ አደሩ ጥሩ ገበያ እንዲያገኝና ምርቱ ጥራት እንዳለው እንዲመሰከርለት ነው››
አቶ በለጠ በየነ የብሌስ አግሪ ፉድ ላቦራቶሪ ሰርቪስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር መሥራችና የቦርድ ሊቀመንበር ናቸው፡፡ በ1969 ዓ.ም. ፋፋ የምግብ ድርጅት ሲመሠረት ጀምሮ በተመጣጠነ ምግብ ማቀነባበር ዙሪያ ተሳትፈዋል፡፡ ከ1985 ዓ.ም. ወዲህ በዚሁ ዘርፍ የግል ድርጅት በመክፈት እየሠሩ ይገኛሉ፡፡