Skip to main content
x
ከኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ጋር የተወያዩ የለገጣፎ ተፈናቃዮች ጥያቄያችን መልስ አላገኘም አሉ
ከኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ጋር የተወያዩ የለገጣፎ ተፈናቃዮች ጥያቄያችን መልስ አላገኘም አሉ
የለገጣፎ ተፈናቃዮች ከኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን ጋር ያደረጉት ውይይት ጥያቄያችንን የሚመልስ አይደለም አሉ፡፡ ‹‹እንወያይ ብለው ሲጠሩን መፍትሔ እናገኛለን ብለን ነበር፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን ማፍረሱ ይቀጥላል ብለውናል፤›› ያሉት አንድ  ተፈናቀይ ‹‹ለምን እንደተጠራን አልገባንም፤›› ብለዋል፡፡
አደጋ የደረሰበትን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን መረጃ መንግሥት ተረከበ
አደጋ የደረሰበትን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን መረጃ መንግሥት ተረከበ
አደጋ በደረሰበት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787-8 ማክስ አውሮፕላን የመረጃ ሳጥን ምርመራ ያካሄደው የፈረንሣይ ቢኢኤ ኩባንያ፣ ያገኘነውን መረጃ ለኢትዮጵያ አደጋ ምርመራ ቢሮ እንዳስረከበ ገለጸ፡፡
በምዕራብ ወለጋ አምስት ሰዎች በጥይት ከተገደሉ በኋላ በቦምብ ተቃጠሉ
በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን በነጆ ወረዳ መንዲ ቶለዋቅ ቀበሌ በመጓዝ ላይ የነበሩ ሦስት ኢትዮጵያውያንና ሁለት የውጭ አገር ዜጎች ማክሰኞ መጋቢት 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ከረፋዱ 1፡30 ሰዓት ላይ፣ በጥይት ተደብድበው ከተገደሉ በኋላ በቦምብ ከእነ ተሽከርካሪያቸው ተቃጠሉ፡፡
መንግሥት አሥር ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ሊገዛ ነው
በአገሪቱ ባጋጠመው ሰብዓዊ ቀውስና በሚሊዮኖች መፈናቀል ምክንያት፣ መንግሥት አንድ ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን (አሥር ሚሊዮን ኩንታል) ስንዴ ግዥ ሊያደርግ መሆኑ ታወቀ፡፡
ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ ተፈጥሮ በነበረ የቡድን ፀብ ምክንያት ታስረው የነበሩ ወጣቶች ተለቀቁ
ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ ተፈጥሮ በነበረ የቡድን ፀብ ምክንያት ታስረው የነበሩ ወጣቶች ተለቀቁ
እሑድ መጋቢት 8 ቀን 2011 ዓ.ም. ከ10፡00 ሰዓት አካባቢ በአንድ የታክሲ ሾፌርና በጫት ነጋዴዎች መካከል የተፈጠረው ጊዜያዊ አለመግባባት፣ በነጋታው ሰኞ መጋቢት 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ወደ ቡድን ፀብ በመሸጋገሩና ኹከት በመፈጠሩ ምክንያት ታስረው የነበሩ ወጣቶች ተለቀቁ፡፡
የሜቴክ የቀድሞ ኃላፊዎች ሰጥተዋል በተባሉበት ሐሰተኛ የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪ ክስ ላይ የእምነት ክህደት ቃል ሰጡ
አሜሪካ ከሚገኘውና ታዋቂ ከሆነው ‹‹ካሊፎርኒያ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ›› ከሚባለው የትምህርት ተቋም ጋር ተቀራራቢ ስም ያለው ‹‹ካሊፎርኒያ ኢንተርናሽናል ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ›› የሚል ሐሰተኛ የፈጠራ ተቋም ስም የተዘጋጀ፣ ሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) እና ሦስተኛ ዲግሪ (ዶክትሬት) ሰጥተዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው የሜቴክ የቀድሞ ኃላፊዎች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፡፡
በይግባኝ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሄደው የአቶ ኤርሚያስ አመልጋ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ
በይግባኝ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሄደው የአቶ ኤርሚያስ አመልጋ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ
ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው በእስር ላይ የሚገኙት የአክሰስ ሪል ስቴትና የዘመን ባንክ መሥራች አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የነፈጋቸውን የዋስትና ሕገ መንግሥታዊ መብት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለማስከበር ይግባኝ ያሉ ቢሆንም፣ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውድቅ አድርጎታል፡፡
ማስታወቂያ

ለዜና መጽሔታችን ደንበኝነት ይመዝገቡ

ዜና መጽሔት
ማስታወቂያ
ማስታወቂያ

ዓለም

ሞዛምቢክ ዚምባቡዌንና ማላዊን የመታው ‹‹ሳይክሎን ኢዳይ››
ሞዛምቢክ ዚምባቡዌንና ማላዊን የመታው ‹‹ሳይክሎን ኢዳይ››
ያለፈው ሳምንት በሞዛምቢክ፣ ዚምባቡዌና ማላዊ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን የፈተነው ከባድ በአውሎ ንፋስና ዝናብ በተያዘው ሳምንት ለዘብ ቢልም፣ በአውሎ ንፋሱ የተጎዱ ሥፍራዎችን ለመድረስ የሚደረገው ጥረት ግን ፈተና ውስጥ ነው፡፡
የፕሬዚዳንት ቡቶፍሊካ ከምርጫ ራሳቸውን ማግለል
የፕሬዚዳንት ቡቶፍሊካ ከምርጫ ራሳቸውን ማግለል
የአልጄሪያው ፕሬዚዳንት አብዱልአዚዝ ቡቶፍሊካ ለሚያዝያ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ተወስኖ የነበረውን የአገሪቱን ምርጫ በማራዘማቸውና ለአምስተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር እንደማይፈልጉ በማሳወቃቸው ለተቃውሞ የወጣው ሕዝብ ድጋፍን ለመግለጽ በአልጄሪያ ጎዳናዎች ተምሟል፡፡
አሜሪካ በዚምባቡዌ ላይ የጣለችው ማዕቀብ መራዘም
አሜሪካ በዚምባቡዌ ላይ የጣለችው ማዕቀብ መራዘም
የዚምባቡዌ ኢኮኖሚ ተዳክሟል፡፡ በዚህም ሳቢያ ሕዝቡ ለችግር መጋለጡ ይነገራል፡፡ አገሪቱ ባለፈው አሥር ዓመት ከነበረው የኢኮኖሚ ቀውስ በከፋ ሁኔታ ውስጥም ትገኛለች፡፡ በአገሪቱ በቂ መጠባበቂያ ገንዘብ የለም፡፡
ሱዳን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ
ሱዳን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ
የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር በአገሪቱ ከሁለት ወር በፊት የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ አስከትሎ የአንድ ዓመት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል፡፡ መንግሥት ነዳጅና ዳቦ ላይ የሚያደርገውን ድጎማ ከሁለት ወር በፊት ማቋረጡን የተቃወሙ ሱዳናውያን፣ በተለያዩ ጊዜያት ተቃውሞ እየወጡ መንግሥትን ሲያስጨንቁ ፕሬዚዳንቱ በሽር ዝምታን መርጠው ነበር፡፡
የናይጄሪያ ምርጫ መራዘም
የናይጄሪያ ምርጫ መራዘም
አብዛኛው ናይጄሪያውያን ባለፈው ቅዳሜ የሚካሄደውን የአገሪቱን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለመሳተፍ ከነበራቸው ጉጉት የተነሳ ከምርጫው አምስት ሰዓት ያህል ቀድሞ የተነገረውን ‹‹የምርጫው ተላልፏል›› ዜና ‹‹የውሸት ዜና ነው›› በሚል ነበር ያለፉት፡፡ ሆኖም ይህ ዜና እውነት ነበር፡፡ ናይጄሪያውያን በጉጉት ሲጠብቁት ነበር የተባለው ምርጫ ለአንድ ሳምንት ያህል ተራዝሟል፡፡
የኢራናውያኑ አብዮት ሲታወስ
የኢራናውያኑ አብዮት ሲታወስ
እ.ኤ.አ. 1979 ለኢራናውያን ልዩ ዓመት እንደነበር ይነገራል፡፡ የኢራናውያን አብዮት የተቀጣጠለበትና ድል የተቀዳጀበት ይኸው ዓመት፣ ኢራን አሁን ላላት ጥንካሬ  መሠረት የተጣለበትም ወቅት ነበር፡፡ ይህ ከሆነ ከትናንት በስቲያ 40 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡

ምን እየሰሩ ነው?

በክር እና በመርፌ የተሠሩ ሥዕሎችን በዐውደ ርዕይ የማሳየት እክል
በክር እና በመርፌ የተሠሩ ሥዕሎችን በዐውደ ርዕይ የማሳየት እክል
ወይዘሮ ሳባ ፀሐዬ የሠዓሊ ንጉሤ ታፈሰ ባለቤት ናቸው፡፡ ባለቤታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ ወደ 18 ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ ወ/ሮ ሳባ፣ ባለቤታቸው በሕይወት በነበሩበት ዘመን የሠሯቸውን ልዩ ልዩ ሥዕሎች በኤግዚቢሽን መልክ ለማቅረብ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡
ለሴቶች ያልተመቹ መኖሪያዎች
ለሴቶች ያልተመቹ መኖሪያዎች
በዓለም አቀፍ ደረጃ አስከፊ በተባለ ሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ የሚገኙትን ለመታደግ እ.ኤ.አ. በ1933 የተመሠረተው ዓለም አቀፉ ሪስኪዩ ኮሚቴ (አይአርሲ)፣ በጤና፣ በደኅንነት፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ እንዲሁም በአስቸጋሪ ግጭት ውስጥና በስደት የሚገኙ ሰዎችን ለመታደግ ይሠራል፡፡
አቅም ለሌላቸው ከተሞች የጤና አገልግሎት ለማስፋፋት የቆመው
አቅም ለሌላቸው ከተሞች የጤና አገልግሎት ለማስፋፋት የቆመው
የሺጥላ ኃይሉ (ዶ/ር) የአምሪፍ ሔልዝ አፍሪካ ምክትል ካንትሪ ዳይሬክተርና የፕሮግራም ኃላፊ ናቸው፡፡ የተወለዱት፣ የመጀመርያና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉት አዲስ አበባ ውስጥ ሲሆን በጎንደር በሕክምና ሳይንስ የመጀመርያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ሠርተዋል፡፡
‹‹ቱሪዝምን ለማሳደግ ቱሪስትን እንብላው የሚለውን አመለካከት መቀየር አለብን›› አቶ ፀጋዬ ተስፋዬ፣ የካኔት ሆቴል (አዳማ) ባለቤት
‹‹ቱሪዝምን ለማሳደግ ቱሪስትን እንብላው የሚለውን አመለካከት መቀየር አለብን›› አቶ ፀጋዬ ተስፋዬ፣ የካኔት ሆቴል (አዳማ) ባለቤት
አቶ ፀጋዬ ተስፋዬ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ የተከታተሉ ሲሆን፣ በወጣትነታቸው ዘመን በተለያዩ አገሮች ኖረዋል፡፡ በተለይ በካናዳ ለረዥም ዓመታት ኖረው ያካበቱትን ጥሪትና የሥራ ልምድ ይዘው ወደ አገራቸው በመመለስ ሪፍት ቫሊ የተሰኘውን ሆቴል በአዳማ ከተማ ገንብተው በ1989 ዓ.ም. ወደ ሥራ ገብተዋል፡፡
‹‹የአርሶ አደሩን የቀደመ ዕውቀትና ሳይንሱን አጣምረን ነው ወደ ሥራ የምንገባው›› አቶ ፋሲል መኳንንት፣ የፀሐይ ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኅበር ማርኬቲንግ ባለሙያ
‹‹የአርሶ አደሩን የቀደመ ዕውቀትና ሳይንሱን አጣምረን ነው ወደ ሥራ የምንገባው›› አቶ ፋሲል መኳንንት፣ የፀሐይ ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኅበር ማርኬቲንግ ባለሙያ
ስድስተኛው አገር አቀፍ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤግዚቢሽን፣ ባዛርና ሲምፖዚየም ከየካቲት 1 እስከ 6 ቀን 2011 ዓ.ም. በኤግዚቢሽን ማዕከል ተካሂዷል፡፡ በሲምፖዚየሙ ከየክልሉ የተውጣጡ የኅብረት ሥራ ማኅበራትና የየክልል የኅብረት ሥራ ኤጀንሲዎች ተካፍለዋል፡፡
‹‹አንድን ተቋም ልዩ የሚያደርገው የተማረ ሰው መያዙ ብቻ ሳይሆን አገልግሎቱ ነው››
‹‹አንድን ተቋም ልዩ የሚያደርገው የተማረ ሰው መያዙ ብቻ ሳይሆን አገልግሎቱ ነው››
ወንድማገኝ ገዛኸኝ (ዶ/ር)፣ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በአገሪቱ ከሚገኙ ነባር ሆስፒታሎች መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በኢትዮጵያ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሕክምና የጀመረ ተቋም ነው፡፡ ከሰሞኑ ደግሞ የመሐንነት ሕክምና መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡