Skip to main content
x
‹‹ሁሉንም ነገር በዜሮ ማባዛትና አፍርሶ የመገንባት አባዜ አገራችንን ወደኋላ ሲጎትት እንጂ ወደፊት ሲያራምድ አላየንም››
‹‹ሁሉንም ነገር በዜሮ ማባዛትና አፍርሶ የመገንባት አባዜ አገራችንን ወደኋላ ሲጎትት እንጂ ወደፊት ሲያራምድ አላየንም››
ሐሙስ የካቲት 7 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ የአገር መከላከያ ሠራዊት ቀን ለሰባተኛ ጊዜ ሲከበር በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት ባለፈው አንድ ዓመት ገደማ ከፍተኛ ለውጥ የተካሄደበት ተቋም መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በ20 ሚሊዮን ብር ለሚገነባው ትምህርት ቤት ቀዳማዊት እመቤት የመሠረተ ድንጋይ አስቀመጡ
በ20 ሚሊዮን ብር ለሚገነባው ትምህርት ቤት ቀዳማዊት እመቤት የመሠረተ ድንጋይ አስቀመጡ
ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘውን የከተሞች ቀን በመገኘት፣ በክልሉ ለሚገነባው የአመንጄ ዮጎል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሠረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡
መጪውን አገር አቀፍ ምርጫ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ ፕሮጀክት ተጀመረ
በሚቀጥለው ዓመት ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀውን አገር አቀፍ ምርጫ አፈጻጸም፣ በከፊል ኤሌክትሮኒክስ ሒደትን የተደገፈ ለማድረግ ፕሮጀክት መጀመሩ ታወቀ፡፡
በመንግሥት ላይ 71.6 ሚሊዮን ብር ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ የቀድሞ የሜቴክ ኃላፊዎች ተከሰሱ
በመንግሥት የተሰጣቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመገልገልና በጥቅም በመመሳጠር፣ በመንግሥት ላይ ከ71.6 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ በሜቴክ ውስጥ የተለያዩ ኃላፊነት የነበራቸው ስድስት ሠራተኞችና አንድ ነጋዴ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው፡፡
በሪል ስቴት  የተሰማሩ ኩባንያዎች የመሬት ሊዝ  ውላቸውን እንዲያድሱ  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሰነ
በሪል ስቴት  የተሰማሩ ኩባንያዎች የመሬት ሊዝ  ውላቸውን እንዲያድሱ  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሰነ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ውስጥ በሪል ስቴት ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች የመሬት ሊዝ ውላቸውን እንዲያድሱ፣ የቤቶች ግንባታ በማካሄድ ላይ ያልሆኑት ደግሞ የሊዝ ውላቸው ተቋርጦ የወሰዱት ይዞታ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ወሰነ።
አቶ ኢሳያስ ዳኘው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ በሰባት አባላት በፀደቀ ውሳኔ ሊጠየቁ እንደማይገባ ተናገሩ
የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት የሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው፣ ኢዲኤም ለተባለ የአሜሪካ አማካሪ ድርጅት ከተፈጸመ ክፍያ ጋር በተያያዘ በሙስና መጠርጠራቸውን ተቃወሙ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጨምሮ በሰባት አባላት በፀደቀ ውሳኔና በተፈጸመ ክፍያ እሳቸው ሊጠየቁ እንደማይገባም ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ እየተካሄደ ላለው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለውጥ አሜሪካ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሆነች አስታወቀች
በኢትዮጵያ እየተካሄደ ላለው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለውጥ አሜሪካ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሆነች አስታወቀች
በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ላለው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለውጥ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኗን አሜሪካ አስታወቀች፡፡
ማስታወቂያ

ለዜና መጽሔታችን ደንበኝነት ይመዝገቡ

ዜና መጽሔት
ማስታወቂያ
ማስታወቂያ

ዓለም

የኢራናውያኑ አብዮት ሲታወስ
የኢራናውያኑ አብዮት ሲታወስ
እ.ኤ.አ. 1979 ለኢራናውያን ልዩ ዓመት እንደነበር ይነገራል፡፡ የኢራናውያን አብዮት የተቀጣጠለበትና ድል የተቀዳጀበት ይኸው ዓመት፣ ኢራን አሁን ላላት ጥንካሬ  መሠረት የተጣለበትም ወቅት ነበር፡፡ ይህ ከሆነ ከትናንት በስቲያ 40 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡
የቬንዙዌላ ቀውስ
የቬንዙዌላ ቀውስ
በቬንዙዌላው ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ እና በተቀናቃኛቸውና የሽግግር መንግሥትነትን ለራሳቸው ባቀዳጁት ሁዋን ጋይዶ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ቬንዙዌላውያንን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ መንግሥታትንም ከፋፍሏል፡፡
የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሽር የግብፅ ጉብኝት
የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሽር የግብፅ ጉብኝት
የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሽር ከግብፅ አቻቸው አብዱል ፈታህ አልሲሲ ጋር ለመምከር እሑድ ጥር 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ወደ ግብፅ አምርተዋል፡፡
እስራኤልና ኢራን በምድረ ሶሪያ
እስራኤልና ኢራን በምድረ ሶሪያ
አሜሪካና ሩሲያ ጎራ ለይተው የእጅ አዙር ጦርነታቸውን የሚያካሂዱባት ሶሪያ ከትናንት በስቲያ (ጥር 12 ቀን 2011 ዓ.ም.)  የእስራኤልን ሚሳይሎች ስታስተናግድ አድራለች፡፡
በዚምባቡዌ ተቃውሞ ያስከተለው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ
በዚምባቡዌ ተቃውሞ ያስከተለው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ
ዚምባቤያውያን የቤንዚንና ናፍጣ ዋጋ መጨመርን ተከትሎ በዚምባቡዌ ዋና ከተማ ሃራሬና በቡላዋዮ ለተቃውሞ ወጥተዋል፡፡ መንግሥት በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጉን ካሳወቀ በኋላ ለተቃውሞ የወጡት ዚምባቤያውያን በየመንገዱ ጎማ ሲያቃጥሉና ድንጋይ ሲወረውሩ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ተስተውለዋል፡፡
የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆን ኡንግ የቻይና ጉብኝት
የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆን ኡንግ የቻይና ጉብኝት
የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆን ኡንግ ለአራት ቀናት ጉብኝት ቻይና ገብተዋል፡፡ ከአሜሪካ ጋር ለሁለተኛ ጊዜ ለመገናኘት ዝግጅት እየተደረገ ባለበት ወቅት ፕሬዚዳንት ኪም ቻይና የገቡት፣ በቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂፒንግ ግብዣ እንደሆነ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ምን እየሰሩ ነው?

‹‹አንድን ተቋም ልዩ የሚያደርገው የተማረ ሰው መያዙ ብቻ ሳይሆን አገልግሎቱ ነው››
‹‹አንድን ተቋም ልዩ የሚያደርገው የተማረ ሰው መያዙ ብቻ ሳይሆን አገልግሎቱ ነው››
ወንድማገኝ ገዛኸኝ (ዶ/ር)፣ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በአገሪቱ ከሚገኙ ነባር ሆስፒታሎች መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በኢትዮጵያ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሕክምና የጀመረ ተቋም ነው፡፡ ከሰሞኑ ደግሞ የመሐንነት ሕክምና መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡
‹‹በኢትዮጵያ 70 በመቶ እናቶች ሳያስቡት ቢያረግዙም እርግዝናውን ይቀበሉታል››  አቶ ዘነበ አካለ፣ የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማኅበር ፕሬዚዳንት
‹‹በኢትዮጵያ 70 በመቶ እናቶች ሳያስቡት ቢያረግዙም እርግዝናውን ይቀበሉታል›› አቶ ዘነበ አካለ፣ የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማኅበር ፕሬዚዳንት
​​​​​​​አቶ ዘነበ አካለ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሚድዋይፍ በመጀመርያ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡ በሶማሌ ክልል ጎዴ ጤና ኮሌጅ ለአራት ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን፣ በደብረ ብርሃን ሪፈራል ሆስፒታል በሕፃናትና እናቶች ክፍል ደግሞ ለሁለት ዓመት ሠርተዋል፡፡
‹‹በወሊድና በቅድመ ወሊድ የሚያጋጥም የደም መፍሰስ በሁለት ሰዓት ውስጥ ይገድላል››
‹‹በወሊድና በቅድመ ወሊድ የሚያጋጥም የደም መፍሰስ በሁለት ሰዓት ውስጥ ይገድላል››
ዶ/ር ተመስገን አበጀ፣ በብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት የደም ለጋሾች ዘርፍ አገልግሎት ዳይሬክተር በኢትዮጵያ የደም ማስተላለፍ ሕክምና የተጀመረው በ1962 ዓ.ም. ለሚሽነሪ ሥራ ወደ ኢትዮጵያ በመጡ እሥራኤላዊ የቀዶ ሕክምና ባለሙያ ነው፡፡
‹‹የተማሪዎች ምገባ በመንግሥት በጀት መካተቱ ትልቅ ስኬት ነው›› ወይዘሪት ሜቲ ታምራት፣ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የሕፃናት ጤናና ምግብ ባለሙያ
‹‹የተማሪዎች ምገባ በመንግሥት በጀት መካተቱ ትልቅ ስኬት ነው›› ወይዘሪት ሜቲ ታምራት፣ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የሕፃናት ጤናና ምግብ ባለሙያ
በአስከፊ ድህነት ውስጥ ከሚገኙ የዓለም አገሮች ተርታ በግንባር ቀደምነት የምትታወቀው ኢትዮጵያ ብዙ አሰቃቂ የድህነት ታሪኮችም የሚሰማባት ምድር ነች፡፡ የዜጎችን መሠረታዊ ፍላጎት ማሟላት አሁንም ድረስ አንገብጋቢ ጥያቄ ነው፡፡
‹‹አሽከርካሪዎች የመጀመርያ ሕክምና ዕርዳታ አሰጣጥን ቢሠለጥኑ የሞት አደጋን መቀነስ ይቻላል›› አቶ ተስፋዬ ንጉሤ፣ የአዲስ አበባ አሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ ተቋማት ማኅበር ፕሬዚዳንት
‹‹አሽከርካሪዎች የመጀመርያ ሕክምና ዕርዳታ አሰጣጥን ቢሠለጥኑ የሞት አደጋን መቀነስ ይቻላል›› አቶ ተስፋዬ ንጉሤ፣ የአዲስ አበባ አሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ ተቋማት ማኅበር ፕሬዚዳንት
አዲስ አበባ ውስጥ 78 የመንግሥትና የግል አሽከርካሪ ማሠልጠኛ ተቋማት ይገኛሉ፡፡ ሕጋዊ ፈቃድ አግኝተው ከሚንቀሳቀሱት ተቋማት መካከል 62ቱ በአዲስ አበባ አሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ ተቋማት ማኅበር ታቅፈዋል፡፡
ከእኩዮቻቸው ወደኋላ የቀሩ ሕፃናትን የመርዳት ጅማሮ
ከእኩዮቻቸው ወደኋላ የቀሩ ሕፃናትን የመርዳት ጅማሮ
ወጣት እመቤት አይቸው የሙዚቃ ትምህርቷን የተከታተለችው በተፈሪ መኮንን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ነው፡፡ በ2010 ዓ.ም. የሦስት ዓመት ትምህርቷን አጠናቃ በአድቫንስድ ዲፕሎማ በኪቦርድ ከተመረቀች በኋላ ትኩረቷን ያደረገችው የትምህርት አቀባበል ችግር፣ የአዕምሮ ውስንነት ወይም ከሌሎች እኩያ ተማሪዎች ጋር በመግባባትና ትምህርት በመቀበል ቀረት የሚሉ ልጆችን ሙዚቃ ትምህርት ብናስተምራቸው ትኩረት የመስጠት ችሎታቸው ይዳብራል፣ ትምህርታቸውም ይቃናል በሚለው ላይ ነው፡፡