Skip to main content
x

ሞዛምቢክ ዚምባቡዌንና ማላዊን የመታው ‹‹ሳይክሎን ኢዳይ››

ያለፈው ሳምንት በሞዛምቢክ፣ ዚምባቡዌና ማላዊ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን የፈተነው ከባድ በአውሎ ንፋስና ዝናብ በተያዘው ሳምንት ለዘብ ቢልም፣ በአውሎ ንፋሱ የተጎዱ ሥፍራዎችን ለመድረስ የሚደረገው ጥረት ግን ፈተና ውስጥ ነው፡፡

የፕሬዚዳንት ቡቶፍሊካ ከምርጫ ራሳቸውን ማግለል

የአልጄሪያው ፕሬዚዳንት አብዱልአዚዝ ቡቶፍሊካ ለሚያዝያ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ተወስኖ የነበረውን የአገሪቱን ምርጫ በማራዘማቸውና ለአምስተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር እንደማይፈልጉ በማሳወቃቸው ለተቃውሞ የወጣው ሕዝብ ድጋፍን ለመግለጽ በአልጄሪያ ጎዳናዎች ተምሟል፡፡

ሱዳን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር በአገሪቱ ከሁለት ወር በፊት የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ አስከትሎ የአንድ ዓመት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል፡፡ መንግሥት ነዳጅና ዳቦ ላይ የሚያደርገውን ድጎማ ከሁለት ወር በፊት ማቋረጡን የተቃወሙ ሱዳናውያን፣ በተለያዩ ጊዜያት ተቃውሞ እየወጡ መንግሥትን ሲያስጨንቁ ፕሬዚዳንቱ በሽር ዝምታን መርጠው ነበር፡፡

የናይጄሪያ ምርጫ መራዘም

አብዛኛው ናይጄሪያውያን ባለፈው ቅዳሜ የሚካሄደውን የአገሪቱን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለመሳተፍ ከነበራቸው ጉጉት የተነሳ ከምርጫው አምስት ሰዓት ያህል ቀድሞ የተነገረውን ‹‹የምርጫው ተላልፏል›› ዜና ‹‹የውሸት ዜና ነው›› በሚል ነበር ያለፉት፡፡ ሆኖም ይህ ዜና እውነት ነበር፡፡ ናይጄሪያውያን በጉጉት ሲጠብቁት ነበር የተባለው ምርጫ ለአንድ ሳምንት ያህል ተራዝሟል፡፡

የኢራናውያኑ አብዮት ሲታወስ

እ.ኤ.አ. 1979 ለኢራናውያን ልዩ ዓመት እንደነበር ይነገራል፡፡ የኢራናውያን አብዮት የተቀጣጠለበትና ድል የተቀዳጀበት ይኸው ዓመት፣ ኢራን አሁን ላላት ጥንካሬ  መሠረት የተጣለበትም ወቅት ነበር፡፡ ይህ ከሆነ ከትናንት በስቲያ 40 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡

የቬንዙዌላ ቀውስ

በቬንዙዌላው ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ እና በተቀናቃኛቸውና የሽግግር መንግሥትነትን ለራሳቸው ባቀዳጁት ሁዋን ጋይዶ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ቬንዙዌላውያንን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ መንግሥታትንም ከፋፍሏል፡፡

በዚምባቡዌ ተቃውሞ ያስከተለው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ

ዚምባቤያውያን የቤንዚንና ናፍጣ ዋጋ መጨመርን ተከትሎ በዚምባቡዌ ዋና ከተማ ሃራሬና በቡላዋዮ ለተቃውሞ ወጥተዋል፡፡ መንግሥት በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጉን ካሳወቀ በኋላ ለተቃውሞ የወጡት ዚምባቤያውያን በየመንገዱ ጎማ ሲያቃጥሉና ድንጋይ ሲወረውሩ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ተስተውለዋል፡፡