Skip to main content
x

ሴቶችን ያንበረከኩ አመለካከቶች

በፆታ እኩልነት ላይ የሚያጠነጥነው የቤጂንግ የትግበራ መርሐ ግብር ከፀደቀ 20 ዓመታት፣ የሚሊኒየሙ የልማት ግብ መተግበር ከጀመረ 15 ዓመታት፣ በአፍሪካ የሚገኙ ሴቶችን መብት ለማስጠበቅ የሚያስችለውን ፕሮቶኮል አፍሪካ ከተቀላቀለች አሥር ዓመታት፣ እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት እ.ኤ.አ. ከ2010 እስከ 2020 የሴቶች ዓመት ብሎ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማሳደግ መሥራት ከጀመረ አምስት ዓመታትን ቢያስቆጥሩም፣ ለአፍሪካ ሴቶች መብታቸው ተከብሮ የመኖር በር ገና አልተከፈተም፡፡

አንገት ከመቅላት ወደ ገንዘብ ድርድር የገባው አይኤስ

ከአንድ ዓመት በፊት በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይህንንም ያህል ዕውቅና ያልነበረው ኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) ዛሬ የለዓለም መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ በተለይ በሶሪያ ላለፉት ሦስት ዓመታት የዘለቀው አለመረጋጋት አድማሱን እንዲያሰፋ አስችሎታል፡፡

ተቃውሞ የበረታበት አወዛጋቢው የኬንያ ፀረ ሽብር ሕግ

ኬንያ የአልሸባብ የሽብር ጥቃት ሰለባ መሆን ከጀመረች ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ የኬንያ መንግሥትም ከአሸባሪዎች እየተሰነዘረበት ያለውን ጥቃት ለመመከት በተደጋጋሚ ቃል ቢገባም አልተሳካለትም፡፡ አልሸባብም ቀድሞ ቦምብ በማፈንዳት ዘር፣ ቀለምና ሃይማኖት ሳይለይ ያደርስ የነበረውን ጥቃት አቅጣጫ በመቀየር በኬንያ ክርስቲያኖች ላይ አነጣጥሯል፡፡ በዚህም ኬንያውያን ሥጋት ውስጥ ወድቀዋል፡፡ መንግሥት የሚገባውን ያህል አልሠራም ሲሉም ኮንነዋል፡፡ የኬንያ መንግሥት በአገሪቱ በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለውን የሽብር ጥቃት ለመግታት ያግዘኛል ብሎ ሰሞኑን የፀረ ሽብር ሕግ ቢያወጣም፣ ከውጭ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ፣ ከውስጥ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ተቃዋሚዎች ሕጉ ሰብዓዊ መብቶችን ይጥሳል ሲሉ ተቃውመዋል፡፡ የፀረ ሽብር ሕጉ ሽብርተኝነትን የመከታተልና የመቆጣጠር፣ የኤሌክትሮኒክስ ግንኙነቶችን የመቆጣጠር፣ የመከታተልና የማቋረጥ መብትን ለደኅንነት አካላት ሰጥቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ማንኛውንም ወንጀል ለመፈጸም ይረዳል ወይም ያገ