Skip to main content
x

የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት በአዲስ ሊተኩ ነው

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ምክትል ሊቀመንበር በመሆን የተመረጡት አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ፣ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በመሆን አቶ ደሴ ዳልኬን እንደሚተኩ ታወቀ፡፡

አቶ ማቴዎስ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር የነበሩትን አቶ ሲራጅ ፈጌሳን ተክተው ማክሰኞ ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. የተመረጡ ሲሆን፣ የድርጅቱ ጽሕፈት ቤትም ከአዲስ አበባ ወደ ክልሉ መዲና ሐዋሳ እንዲዛወር ተወስኗል፡፡

የድርጀቱ ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤም ከሊቀመንበርነታቸው ተነስተው፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል መተካታቸው ይታወሳል፡፡