Skip to main content
x
ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ራሳቸውን እንዳጠፉ ተገለጸ

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ራሳቸውን እንዳጠፉ ተገለጸ

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሸነር ዘይኑ ጀማል ከጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተወካዮች ጋር በመሆን ዓርብ ጳጉሜን 2 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሕይወታቸው ያለፈው በሌላ አካል ጥቃት ደርሶባቸው ሳይሆን ራሳቸውን አጥፍተው ነው ሲሉ አስታወቁ፡፡

ኢንጂነሩ ከመሞታቸው በፊት ከጸሐፊያቸው ጋር ባደረጉት የስልክ ንግግር፣ እሳቸው በጻፉት ደብዳቤና በፎረንሲክ ምርመራ ራሳቸውን መግደላቸው ተረጋግጧል ብለዋል፡፡