Skip to main content
x

በአፍሪካ የጤና ዘርፍ የ66 ቢሊዮን ዶላር የበጀት ጉድለት መኖሩ ተጠቆመ

 በአፍሪካ የጤና ዘርፍ ላይ በሚመክረው ‹‹የአፍሪካ ዝነስ ሔልዝ ፎረም 2019›› በአኅጉሪቱ በየዓመቱ 66 ቢሊዮን ዶላር ለጤና አገልግሎት የሚያስፈልግ የበጀት ጉድለት እንደሚታይ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ቬራ ሶንግዌ (/) አስታወቁ። 

በአፍሪካ  በግሉና በመንግሥት አጋርነት በኩል እስከ 450 ቢሊዮን ዶላር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚያስገኙ ዕድሎች እንዳሉም አስታውቀዋል።  በኢትዮጵያም የዚህ ዓይነቱ አጋርነት ላይ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ዝግጅት እየተደረገበት እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (/) ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ከፍተኛ ደረጃ ያለውና በኢኖቬሽን የታገዘ የጤና ምርመራ አገልግሎት በጥቁር አንበሳና በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታሎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል። 

ኢትዮጵያ ከሚሊኒየሙ የልማት ግቦች ከአምስት ዓመት በታች የሕፃናት ሞትን በሁለት ሦስተኛ መጠን በመቀነስ ግቡን ከሦስት ዓመታት ቀድማ ማሳካቷን፣ በጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች አማካይነትም የጤና አገልግሎቶችን 70 በመቶው ሕዝብ ማዳረስ ስለመቻሏ በማውሳት፣ ‹‹ጤና ይስጥልኝ›› በማለትና ለታዳሚያኑ በማብራራት የጀመሩትን ንግግር በጤና ይስጥልኝ ዘግተዋል። 

የጅቡቲና የቦትስዋና ፕሬዚዳንቶች፣ የግብፅና የኬንያ ጤና ሚኒስትሮችም ስለየአገሮቻቸው ጤና ዘርፍ ተናግረዋል። የአሊኮ ዳንጎቴ ልጅ ሐሊማ ዳንጎቴም የአባቷ ፋውንዴሽን ስለሚያከናውናቸው እንቅስቃሴዎች ገልጸዋል።