Skip to main content
x
መንግሥት በቆርኪና ጣሳ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ላይ የነበረውን ሙሉ ይዞታ በ130 ሚሊዮን ብር ሸጦ ወጣ
ከግራ፡ አቶ በየነ ገብረመስቀል ከሲ.ጂ.ኤፍ ግሩፕ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ግርማይ ፈረደ ጋር የሽያጭ ስምምነቱን በፈረሙበት ወቅት

መንግሥት በቆርኪና ጣሳ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ላይ የነበረውን ሙሉ ይዞታ በ130 ሚሊዮን ብር ሸጦ ወጣ

መንግሥት በኢትዮጵያ ቆርኪና ጣሳ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ክሲዮን ማኅበር ላይ የነበረውን 75 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ በ130 ሚሊዮን ብር በመሸጥ ሙሉ ለሙሉ ይዞታውን ለግል ኩባንያ አስረከበ፡፡

የሽያጭ ውሉ ማክሰኞ፣ መጋቢት 3 ቀን 211 .ም. በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲና ጂሲኤፍ ቢዝነስ ግሩፕ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በተሰኘው የግል ኩባንያ መካከል ሲፈረም፣ በውሉ መሠረት ኤጀንሲው ሙሉ ለሙሉ ይዞታውን አስረክቦ እንደሚወጣ ታውቋል፡፡ የሽያጭ ስምምነቱን የፈረሙት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ በየነ ገብረመስቀል ሲሆኑበገዥው ሲጂኤፍ በኩል ደግሞ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ግርማይ ፈረደ ናቸው፡፡

መንግሥት በቆርኪና ጣሳ  አክሲዮን ማኀበር ላይ የነበረውን ድርሻ ሙሉ በሙሉ ወደ ግል ባለሀብቶች ለማዘዋወር ከዚህ በፊትተደጋጋሚ የጨረታ ማስታወቂያ ሲያወጣ መቆየቱን ለሪፖርተር በላከው መግለጫ ያስታወሰው ኤጀንሲው፣ ባለፈው ዓመት አውጥቶ በነበረው ጨረታ (ጨረታ ቁጥር ዐዐ1/217-218)፣ አዲሱ ባለድርሻ ጂሲኤፍ ቢዝነስ ግሩፕ ብቸኛ ተጫራች በመሆን ቀርቦ ነበር፡፡ ኩባንያው የመንግሥትን ድርሻ ለመጠቅለል 13 ሚሊዮን ብር ዋጋ አቅርቦም እንደነበር ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡

ለመንግሥት የቀረበለት የግዥ የአክሲዮን ድርሻውን ለመሸጥ ካወጣው 125.9 ሚሊዮን ብር ጠቋሚ ዋጋ አኳያ ብልጫ ያለው በመሆኑ፣ ሽያጩ ፀድቆገዥው የሚጠበቀውን የ35 በመቶ የቅድሚያ ክፍያ ዋጋውን (45.5 ሚሊዮን ብር) ኩባንያው ገቢ በማድረጉ የሽያጭ ውሉ እንደተፈረመ የኤጀንሲው መግለጫ ይጠቁማል፡፡ ኩባንያው ቀሪውን 65 በመቶ ክፍያ በአምስት ዓመታት ውስጥ ከፍሎ ለማጠናቀቅ መስማማቱን በሽያጩ ወቅት ተጠቅሷል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ በየነ ገብረመስቀል ከፊርማ ሥነ ሥርዓቱ በኋላ ባደረጉት ንግግር፣ ሲጂኤፍ ቢዝነስ ግሩፕ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር የአክሲዮን ማኀበሩን ከፍተኛ ድርሻ እንደመግዛቱ መጠን፣ ድርጅቱን በአሁኑ ወቅት ከሚገኝበት ደረጃ የበለጠ የማሳደግ ኃላፊነት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

የሲጂኤፍ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ግርማይ ፈረደ በበኩላቸው፣ መንግሥት ባካሄዳቸው የፕራይቬታይዜሽን ክንውኖች ውስጥ በመሳተፍና የመንግሥት የልማት ድርጅትን ሲገዙ የመጀመሪያቸው እንዳልሆነ ጠቅሰው፣ የኤጀንሲው የድኀረ ፕራይቬታይዜሽን ክትትልና ድጋፍ እንዳይለያቸው አሳስበዋል፡፡ ሲጂኤፍ ቢዝነስ ግሩፕ በጥራጥሬ ወጪ ንግድ፣ በምግብ ዘይት አስመጪነት፣ በሆቴል ንግድ ሥራ እንዲሁም በቆርኪ ማምረቻ፣ በሕክምና ጓንት፣ በሪል ስቴት፣ በፒፒ ከረጢት፣ በጭነት ተሽከርካሪዎች፣ በጣሪያ ታይልስ ማምረቻና በሌሎችም ዘርፎች ውስጥ እየተሳተፈ የሚገኝ አገር በቀል ኩባንያ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በአሁኑ ወቅት በእጁ ከሚገኙ የልማት ድርጅቶች ውስጥ ለሽያጭ ያቀረበው ድርጅት ባይኖርም፣ የከንጢቻ የማዕድን ማምረቻን በጋራ ለማልማት ፍላጎት ላላቸው የግል ኩባንያዎች ጥሪ ማቅረቡንና ምላሽ እየተጠባበቀ እንደሚገኝ ከኤጀንሲው የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽንስ ዳይሬክተር አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ ለመረዳት ተችሏል፡፡