Skip to main content
x
የሶማሌና የኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ችግሩ መፍትሔ ሲያገኝ ወደ ቀድሞ ዩኒቨርሲቲያቸው እንደሚመለሱ ተገለጸ

የሶማሌና የኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ችግሩ መፍትሔ ሲያገኝ ወደ ቀድሞ ዩኒቨርሲቲያቸው እንደሚመለሱ ተገለጸ

በዳዊት እንደሻው

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የሁለቱ ክልሎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በየክልሎቻቸው እንዲመደቡ የተደረጉት በትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ እንጂ በክልሎች ጣልቃ ገብነት አይደለም ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ጥላዬ ጌቴ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡

በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እንደገና የተመደቡት የሁለቱ ክልሎች ተማሪዎች “ችግሩ መፍትሄ ሲያገኝ ወደ ነበሩበት ዩኒቨርሲቲዎች ይመለሳሉ፤” ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ክልሎች በዩኒቨርሲቲዎች ላይ ምንም ዓይነት የመወሰን ሥልጣን የላቸውም ያሉት ሚኒስትሩ እስካሁንም ክልሎች ጣልቃ ገብተው ያስተላለፉት ውሳኔ የለም ብለዋል፡፡ “የወሰንነው እኛው እና እኛው ነን” ሲሉም አክለዋል፡፡