Skip to main content
x
የአፍሪካ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንትነትን ያገኘችው ኢትዮጵያ

የአፍሪካ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንትነትን ያገኘችው ኢትዮጵያ

ከግማሽ ምዕት በላይ ዕድሜ ባስቆጠረው የአፍሪካ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር ላለፉት አራት ዓመታት በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት ስትሳተፍ የነበረችው ኢትዮጵያ፣ ሰሞኑን በኬንያ ናይሮቢ በተደረገው ጉባዔ ምክትል ፕሬዚዳንትነት አግኝታለች፡፡ የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ዮናስ ተሾመ ከአህጉራዊው ማኅበር ከሥራ አስፈጻሚ አባልነት ወደ ምክትል ፕሬዚዳንትነት አድጓል፡፡ ናይጄሪያዊው ሚሼል አቢ በፕሬዚዳንትነት ሲመረጥ፣ ከአራት ምክትሎች አንዱ ከምሥራቅ አፍሪካ የኢትዮጵያው ዮናስ ለመመረጥ ችሏል፡፡ አህጉራዊ ማኅበር በአፍሪካ ጋዜጠኞች መካከል ኅብረት የመፍጠር፣ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችና ዐውደ ጥናቶች በመስጠት እንደሚቀንቀሳቀስ፣ ብሔራዊ ማኅበሩም የአገሪቱን የስፖርት ጋዜጠኞች ባንድ ጥላ ሥር በማሰባሰብ ሙያው የሚበለጽግበትን ተግባሩንም እንደሚወጣ አቶ ዮናስ ለሪፖርተር ገልጿል፡፡ መቀመጫውን በሞሮኮ ካዛብላንካ ከተማ ያደረገው የአፍሪካ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር በ1960ዎቹ መጀመርያ ሲቋቋም፣ ከመሥራቾቹ አንዱና መሪ የነበረው ፍቅሩ ኪዳኔ 6ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በአዲስ አበባ ሲዘጋጅ በተካሄደው ጉባዔ መመረጡ ይታወሳል፡፡ ፎቶው ተመራጮቹ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን የሚያሳይ ሲሆን ከቆሙት ከቀኝ ሦስተኛው ኢትዮጵያዊው ዮናስ ተሾመ ነው፡፡