Skip to main content
x
ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ  (1973-2010)

ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ (1973-2010)

ያለ ዕድሜያቸው የሕይወት ጀምበር ከጠለቀባቸው ወጣቶች አንዱ በስፖርቱ ዘርፍ ስሙ የሚጠቀሰው ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ ነው፡፡

ጋዜጠኛ ኢብራሒም የእግር ኳስ ስፖርታዊ ትንታኔዎችን በመስጠትና በኅትመት ውጤቶች ላይ ከመጻፍ ባሻገር፣ በኤሌክትሮኒክስ ቀጥታ ሥርጭት ወቅት የሚያቀርባቸው በሳል ሐሳቦች በብዙዎች ዘንድ ቦታ እንዲያገኝ አስችለውታል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ አካባቢ ተወልዶ ያደገው ኢብራሂም፣ በፖለቲካ ሳይንስና በዓለም አቀፍ ግንኙነት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢመረቅም፣ ወደ ስፖርት በማድላት የሕይወቱን አብዛኛውን ክፍል ያሳለፈው ለስፖርት ካለው ጥልቅ ፍቅር በመነሳት እንደሆነ ባልንጀሮቹ ይናገሩለታል፡፡

የሙያ አጋሩና አብሮ አደጉ ጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ፣ የኢብራሂም ሻፊን ዜና ዕረፍት በማስመልከት በሬዲዮ ፕሮግራሙ ከሠራው ትውስታ ለመገንዘብ እንደተቻለው፣ ወጣቱ ኢብራሂም ለአቋሙ ጽኑና ላመነበት ሟች ነበር፡፡ ለበርካታ ዓመታት በስፖርት ጋዜጠኝነት በጋዜጦችና በሬዲዮ ፕሮግራሞች  ሲሳተፍ የቆየበት ምክንያትም ከዚሁ የመነጨ መሆኑ ይነገርለታል፡፡

በስደት በኖረባት ኬንያ ታኅሣሥ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ያረፈው ኢብራሂም ሥርዓተ ቀብር ታኅሣሥ 27 ቀን በኮልፌ የእስላም መካነ መቃብር ተፈጽሟል፡፡