Skip to main content
x
ሎሚ!

ሎሚ!

ሎሚ የታወቀ ተክል ሽታው የሚጣፍጥ ለሥራይና ለመርዝ መድኀኒት የሚኾን ዕንጨቱም ፍሬውም ሎሚ ይባላል፤ ይላል ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት፡፡ ጥር ወርና ሎሚን የሚያገናኛቸው የሚያቆራኛቸው በወሩ ውስጥ የሚውለው የጥምቀት በዓል ነው፡፡ ኮረዳና ኮበሌን በፍቅር ያገናኛል፡፡ በጨዋታ መሃል ‹‹ሎሚ ውርወራ›› የሚባል ነገር አለ፡፡ ቀልቡ የሚፈቅዳትን ልቡ የከጀላትን ‹‹ወለላዬ›› ብሎ ሎሚ ይወረውርላታል፡፡ ለዚህም ይመስላል ሎሚ ፍቅር ማጣፈጫ የሚሉት፡፡

‹‹ሎሚ ሁለገብ ጥቅም አለው›› የሚለው ጄደብሊው የተሰኘው ድረገጽ ላይ የወጣው መጣጥፍ ነው፡፡ እንዲህም ይለጥቃል፡- ሎሚ ለመድኃኒት፣ ለጽዳት አገልግሎት፣ ጀርሞችን ለመግደልና ውበትን ለመጠበቅ ያገለግላል። ልትበላው፣ ጨምቀህ ልትጠጣው እንዲሁም ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ለማውጣት ልትጠቀምበት ትችላለህ። ሲያዩት የሚያምር ከመሆኑም በላይ በሁሉም የዓለም ክፍሎች ይገኛል፤ ዋጋውም ቢሆን ርካሽ ነው። አሁን ራሱ ቤትህ ውስጥ ሊኖር ይችላል። ይህ ነገር ምን ይሆን? ሎሚ ነዋ!

  • ሔኖክ መደብር