Skip to main content
x

ከሃሎዊን ጋር የሚመሳሰሉ በዓላት

ኢንሳይክሎፒዲያ ኦፍ አሜሪካን ፎክሎር እንደሚለው  “ሃሎዊን ከመንፈሳዊ ፍጥረታት ጋር ለመገናኘት ታስቦ የሚደረግ ክብረ በዓል ነው፡፡ አብዛኞቹ ፍጥረታት ደግሞ የሚያስፈሩና የሚያስደነግጡ ናቸው፡፡”

ሃሎዊን በአብዛኛው የሚታወቀው የአሜሪካውያን በዓል እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ በዓል በብዙ የዓለም ክፍሎች ተወዳጅ እየሆነ መጥቷል፡፡ በተጨማሪም ከሃሎዊን ጋር ተመሳሳይ የሆኑና በመንፈሳዊ ፍጡራንና በእንቅስቃሴያቸው ላይ የሚያተኩሩ ሌሎች በዓላት አሉ፡፡ በዓለም ዙሪያ ከሚከበሩና ከሃሎዊን ጋር ከሚመሳሰሉ በርካታ በዓላት መካከል የሰሜን አሜሪካ የሙታን ቀን፣ የአውሮፓ የሙታን ቀንና በሌላ ስያሜ የሚጠሩ የሃሎዊን በዓላት፣ የእስያ የቦን ክብረ በዓል፣ የደቡብ አሜሪካ ካውሳስካንቺስ እና የአፍሪካ ኤገንገን የሚባሉ የተከናነቡ ሰዎች የሚያደርጉት ጭፈራ ይገኙበታል፡፡