Skip to main content
x
የእንቁራሪቶች መጠንና ጥፍጥና

የእንቁራሪቶች መጠንና ጥፍጥና

እንቁራሪቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለምግብነት ጥቅም ላይ በመዋል የታወቁ ናቸው ይላል በማንይንገረው ሸንቁጥ የተጻፈው ‹‹ባለአከርካሪዎች›› መጽሐፍ፡፡ እንቁራሪቶች  ለምግብነት ከሚውለው የአካላቸው ክፍል በዋነኝነት የኋለኛ እግራቸው በጣፋጭነቱ ይጠቀሳል፡፡ ከእንቁራሪቶች በተጨማሪ ሳላማንደር በጃፓንና ተዘውታሪ ምግብ ነው፡፡

በጃፓንና በቻይና የሚገኘው ከ1 ሜትር በላይ ርዝመትና 40 ኪሎ ግራም ክብደት ያለው ሳላማንደር በትልቅነቱ ይታወቃል፡፡ በምዕራብ አፍሪካ በተለይም በካሜሮን የሚገኘው ትልቁ እንቁራሪት ከ30 እስከ 33 ሳንቲ ሜትር ርዝመት እንዳለው ሲገመት የኋላ እግሩ ርዝመትም ስለሚበልጥ በአጠቃላይ ርዝመቱ ከ60 ሳንቲ ሜትር በላይ ይሆናል፡፡ ይህን እንቁራሪትም ካሜሮኖች ለምግብነት ይጠቀሙበታል፡፡ በአሜሪካ ደግሞ ትልቁ ሳላማንደር ወደ 1 ሜትር ርዝመት ሲኖረው ከእንቁራሪቶቹ ደግሞ እስከ 20 ሴንቲ ሜትር ርዝመት እንደሚደርስ ይታወቃል፡፡ በጠንም ሆነ በዝርያ ብዛትም አነስተኛ የሆኑት ደግሞ እግር የለሾቹ ሴሲሊያን ናቸው፡፡