Skip to main content
x
ምግብ አስተዋዋቂው የ18 ወር ሕፃን

ምግብ አስተዋዋቂው የ18 ወር ሕፃን

የኦቲዝም ተጠቂ የሆነው የ18 ወር ዕድሜ ያለው ሕፃን ምግብ የሚያመርተው የገርበር ኩባንያ አዲስ ፊት ሆኖ እንዲያስተዋውቅ ተመረጠ፡፡

ሕፃኑ ሉቃስ ዋርን ከ140 ሺሕ ሕፃናት መካከል የተመረጠው የኦቲዝም እክል ተጠቂዎች በማኅበረሰቡ ዘንድ የሚኖራቸውን ተቀባይነት እንደሚጨምር ታምኗል፡፡ 50 የሉቃስ ቤተሰቦች 50,000 ዶላር የሚከፈላቸው ሲሆን፣ ፎቶውም በገርበር ማኅበራዊ ሚዲያ ገጽና በተለያዩ የድርጅቱ ማስታወቂያዎች ላይ ይሠራጫል፡፡ ‹‹በዚህ ዓመት የሉቃስ ደስተኛ ፊትና አስደናቂ ፈገግታ ልጃችን አሸንፏል፤›› ያለው የገርበር ዋና ሥራ አስፈጻሚና ፕሬዚዳንት ቢል ፐርቲካ ነው፡፡ የሉቃስ መመረጥም ሁሉም ልጆች የገርበር ልጆች መሆናቸውን ማሳያ ነው ማለቱን የዘገበው ያሆ ኒውስ ነው፡፡