Skip to main content
x
በሐረሪ - ሐማሬሳ በተፈጠረ ግጭት አራት ሰዎች ሕወታቸውን አጡ

በሐረር ከተማ ሐማሬሳ በተፈጠረ ግጭት አራት ሰዎች ሕወታቸውን አጡ

በሐረር ከተማ ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን አስጠልሎ በሚገኘው የማሬሳ መጠለያ ጣቢያ ትናንት የካቲት 4 ቀን 2010 ዓ.ም. በወጣቶችና በፀጥታ አካላት መካከል በተፈጠረ ግጭት አራት ግለሰቦች መሞታቸውና አሥር ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ታወቀ፡፡

ከሞቱት ውስጥ ሦስቱ በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሲሆን አንዱ ደግሞ የኦሮሚያ ፖሊስ አባል መሆኑ ታውቋል፡፡

ለጣቢያው ቅርብ ከሆኑ ምንጮች ሪፖርተር ማረጋገጥ እንደቻለው ተጎጂዎቹ በአሁን ወቅት ሐረር ከተማ በሚገኘው ሕይወት ፋና ሆስፒታል ሕክምና እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡

በዛሬው ዕለት በመጠለያ ጣቢያው የተሻለ አንፃራዊ መረጋጋት እንዳለም ታውቋል፡፡ በሐማሬሳ መጠለያ ጣቢያ ከሦስት እስከ አራት ሺሕ የሚሆኑ ተፈናቃዮች እንደተጠለሉ ይገመታል፡፡