Skip to main content
x
ፍሬ ከናፍር

ፍሬ ከናፍር

‹‹ኢትዮጵያ በሕዳሴ ግድብ ላይ የሚደረገው ውይይት እንዲተላለፍላት እንድትጠይቅ ያስገደዳትን ሁኔታ እንረዳለን፡፡››

የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አህመድ አቡዘይድ፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙርያ በሳምንቱ መጨረሻ በካርቱም ሱዳን ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለት የነበረው የኢትዮጵያ ሱዳንና ግብፅ ሦስትዮሽ ውይይት ኢትዮጵያ እንዲተላለፍላት መጠየቋን ተከትሎ ለሚዲያ የተናገሩት፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከሥልጣን መልቀቅ ተከትሎ ለስድስት ወር የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰበብ የሆነበት የካቲት 17 እና 18 ቀን 2010 ዓ.ም. የሦስትዮሹ ስብሰባ፣ ወደፊት በተቻለ ሁኔታ ሊካሄድ እንደሚችል እምነታቸው እንደሆነ የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መናገራቸውም ተዘግቧል፡፡