Skip to main content
x
ኦሕዴድ ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሊቀ መንበር አድርጎ መረጠ
ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)

ኦሕዴድ ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) ሊቀ መንበር አድርጎ መረጠ

የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) ሊቀ መንበር አድርጎ መምረጡን በፓርቲው ይፋዊ የፌስ ቡክ ገጽ አስታወቀ፡፡ ዶ/ር ዓብይ የሊቀ መንበርነት ሥልጣኑን ከአቶ ለማ መገርሳ በዛሬው እለት የተረከቡ ሲሆን አቶ ለማ የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው እንደሚቀጥሉ ታውቋል፡፡

ዶ/ር ዓብይ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የፓርቲው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ እንደቆዩ ይታወሳል፡፡