Skip to main content
x
በአዲስ አበባ የሚገኘው ኤኮን

በአዲስ አበባ የሚገኘው ኤኮን

ታዋቂው የአሜሪካ አርሲቢ (RCB) የሙዚቃ ስልት አቀንቃኝ ኤኮን ሐሙስ የካቲት 22 ቀን 2010 ዓ.ም. አዲስ አበባ ገብቷል፡፡ ከኢትዮጵያዊት ባለቤቱ ሮዚና ንጉሤ ጋር በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን ከዋሽንግተን ዲሲ የመጣው ኤከን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ በአየር መንገዱ ኃላፊዎች፣ የአፍሪካ ኅብረት ተወካዮችና ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ በቪአይፒ ሳሎን በተደረገለት ግብዣ ‹‹ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ ቤቴ እንዳለሁ ይሰማኛል›› ያለው ኤኮን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር በማገናኘት ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሆነ ገልጿል፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምርጫዬ ነው፤›› ሲልም አክሏል፡፡ ኤኮን በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ ተገኝቶ ለአፍሪካ ወጣቶች ስደትን አስመልክቶ ዲስኩር አሰምቷል፡፡