Skip to main content
x

አገር ሊወድቅና ሊነሳ የሚችለው መንግሥት በሚተገብረው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው!

እንደገና ወደ ማክሮ ኢኮኖሚ ጽንሰ ሐሳብ እንምጣ። ይህንን በንጽጽር (Analaogy) እንመልከተው። ከላይ ለማሳየት እንደ ሞከርኩት ማክሮ ማለት ትልቅ ነገር ማለት ነው። እንደሚታወቀው  ማንኛውም ግዙፍ ወይም ትልቅ ነገር የትናንሽ ንጥረ ነገሮች ክምችት ነው።

አገር ሊወድቅና ሊነሳ የሚችለው መንግሥት በሚተገብረው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው!

በኢትዮጵያና በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ውስጥ በግልጽ የሚታዩት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውሶች ሥር ከሰደደ የተቋም ቀውስ ጋር የተያያዙ ናቸው። ይህ ዓይነቱ የተቋም ቀውስ በድህነት፣ በቆሻሻ መኖሪያ ቦታዎች፣ በድብቅና ግልጽ በሆነ መልክ የሚገለጽ የሥራ አጥነት፣ በከተማዎች መጨናነቅና በንፁህ ውኃ ዕጦት የተነሳ ጎልቶ የሚታይ ነው።

‹‹የገፓት ቃዋ›› - የጉራጌዎች የሸንጎ ቡና                   

ጉራጌዎች መሸት ሲል ተጠራርተው የሚጠጡት ቡና ‹‹የገፓት ቃዋ›› እያሉ ይጠሩታል፡፡ እናቶች ተራቸውን ጠብቀው ቃዋ ያፈላሉ፡፡ በገፓት ቃዋ ድርድር የላቸውም፡፡ ከበድ ያለ ችግር እንኳ ቢያጋጥማቸው ተራቸውን ውልፍት አያደርጉትም፡፡

አገር ሊወድቅና ሊነሳ የሚችለው መንግሥት በሚተገብረው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው!

አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች ነፃነትን ከተቀዳጁ ከሃምሳ ዓመት በኋላ በድህነት ዓለምና በጥገኝነት ውስጥ የሚገኙ ናቸው። በአብዛኛዎቹ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ የተትረፈረፈ የጥሬ ሀብትና እንዲሁም ለነዳጅ የሚሆን ዘይትና ጋዝ ቢኖርም ሕዝቦቻቸው በድህነት ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ናቸው።

ድረሱልኝ የሚለው ቅዱስ ላሊበላ የላስታው ደብር

በሥነ ትምህርት ዘርፍ የተሰማሩ ምሁራን ትምህርትን በሁለት ይከፍሉታል፤ መደበኛና ኢመደበኛ በማለት፡፡ መደበኛ የሚሉት በተደራጀ፣ በተቀነባበረና ሥርዓት ባለው መልክ በትምህርት ቤት ውስጥ የሚሰጠውን ዕውቀት ሲሆን፣ ኢመደበኛ የሚሉት ደግሞ ግብታዊ በሆነ መንገድ ከአካባቢ፣ ከሥራ ልምድና ከሕይወት ገጠመኝ የሚቀሰመውን ነው፡፡

‹‹ያጋ ቃዋ››- የጉራጌዎች የቡና አጠጣጥ ሥነ ሥርዓት

ጉራጌዎች ማኅበራዊ ግንኙነታቸውን ከሚያቀራርብላቸው ወይም ከሚያጠነክርላቸው መልካም እሴቶች መካከል ‹‹ያጋ ቃዋ›› የሚሉት የቡና አጠጣጥ ሥነ ሥርዓት አንዱ ነው፡፡ የጉራጌ ማኅበረሰብ ካለበት ቀዬ አቅራቢያ ከሚገኙ ጎረቤቶቹ ከሦስት እስከ ስድስት አባላት በመሆን ቃዋ (ቡና) ይጠጣሉ፡፡

‹‹ሁሉም አካላት [ለላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት]  አስፈላጊውን ድጋፍና ቅንጅት እንዲያረጋግጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን›› የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን

እንደሚታወቀው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ከዕድሜ ርዝመት እንዲሁም የተለያዩ ተፈጥሮአዊና ሰው ሠራሽ ምክንያቶች በተለያየ ደረጃ የእርጅናና የስንጥቅ ጉዳት ይስተዋልባቸዋል፡፡ የጥገና ፍላጎትን መሠረት ተደርጎ ላለፉት ዓመታት የተለያዩ የጥገና ትግበራ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

ግምገማዊ አስተያየት በተናፋቂ ትዝታዎቻችን

በተሾመ ብርሃኑ ከማል የመጽሐፉ ርዕስ - ተናፋቂ ትዝታችን የመጽሐፉ ደራሲ - ኮሎኔል መለሰ ተሰማ የመጽሐፉ ገጽ - 232 ኤ5 መጠን መጽሐፉ የክብር ዘበኛ አካዴሚ ሁለተኛ ኮርስ አባላትንና የኮሪያ ጦርነትን የሚያመለክቱ ፎቶግራፎችን ይዟል፡፡ የዘማቾች የስም ዝርዝርም ተካቶበታል፡፡

የአገራችን የትምህርት ጥራት ውድቀት በቀላሉ የሚታይ አይደለም

ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ጥራት መውደቅ ውጫዊና ውስጣዊ ነገሮች ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ውጫዊው አስቀድሜ የጠቀስኩት የመንግሥት አላስፈላጊ ውሳኔዎች፣ የተማሪው ቅድመ ዝግጅትና አስተሳሰቡ፣ የተማሪዎች መብዛት፣ በዚያው ልክ ብቃት ያላቸው መምህራን አለመኖር፣ ቤተ ሙከራዎች አለማዳረስ ወዘተ. ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡