Skip to main content
x

የሰብዓዊ ክብር ውርደትን ለመታደግ ከሚያስፈልጉ አሠራሮችና ሕጎች መካከል

ሰሞኑን የሕዝብ አጀንዳ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል  በማረፊያና በማረሚያ ቤቶች ሲፈጸም የነበረው ዘግናኝና ሰቅጣጭ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አንድኛው ነው፡፡ በተለይም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን)፣ በአማራ ቴሌቪዥንና በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የቀረበውን ወይም የተላለፈውን መጥቀስ ይችላል፡፡

ፈተና ላይ የወደቀው የንግድ ሕግ ነፃነት

የአንድ አገር የሕግ አደረጃጀት በሰፊው ሲታይ የሕዝብና የግል ሕግ ተብሎ ይከፈላል፡፡ እነዚህ ራሳቸው ደግሞ የተለያዩ ክፍልፋዮች ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ከእነዚህ ሕጎች መካከል በአብዛኛው በግል ሕግ የሚመደበው የንግድ ሕግ ነው፡፡ የንግድ ሕግ የሲቪል ሕግ አካል ሆኖ ያደገና ቤተሰብ የሆነ ነው፡፡

የአዲስ ክልል አመሠራረት ሕግ የሲዳማ ጥያቄ እንደመነሻ

ሰሞኑን በወልቂጤ፣ በወላይታ ሶዶና በሐዋሳ ከተማ በተከሰቱ ግጭቶች የሰው ሕይወት መጥፋቱ፣ የአካል ጉዳት መድረሱና ንብረት መውደሙ ይታወቃል፡፡ የሚያመሳስላቸው ቢኖርም የግጭቶቹ መንስዔዎች የሚያለያያቸው ባህሪያት መኖሩ ግልጽ ነው፡፡

እስላማዊ ባንክ በኢትዮጵያ የሕግ መነጽር

አሁን ላይ በብዙ ደርዘን የሚቆጠሩ አገሮች ሸሪዓን አክብረውና በዚሁ መሠረት ብቻ ተወስነው የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት አሉ፡፡ እነዚህ ባንኮች ደግሞ ከዓረቡ ዓለምና ከእስላማዊ አገሮች በተጨማሪም በምዕራቡ ዓለምም ዘንድ ከታወቁና ከተለመዱ ሰነባብተዋል፡፡

የሕግ ሚና በልማታዊ መንግሥት

ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ አገራችንን በሚመለከት ከተፈጸሙ ጉዳዮች መካከል የሕዝብን ትኩረት በከፍተኛ ሁኔታ የሳበው የገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ያደረገችው የአልጀርስን ስምምነትና እሱን ተከትሎት የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ መቀበሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ድርጅትና የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨትን ከፍተኛውን የአክሲዮን ድርሻ (51 በመቶ) መንግሥት ይዞ ቀሪውን አክሲዮን ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች በሽያጭ እንዲተላለፍ መወሰኑ እንዲሁም በርካታ በመንግሥት ሥር የሚተዳደሩ የልማት ድርጅቶችን ደግሞ ሙሉ በሙሉ ለአገር ውስጥም ይሁን ለውጭ ባለሀብቶችም መንግሥታትም እንዲሸጡ መወሰኑ ነው፡፡

የመንግሥት በሕግ መመራት ሕዝብ በሕግ ላይ ያለውን ዋስትና ለመታደግ

ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በኋላ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ቀድሞ ከተለመደው አሠራር ለየት ያሉ ዕርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡  ብሔራዊ መግባባት መፍጠርም ዋና ትኩረት ያደረጉበት አጀንዳ ይመስላል፡፡ የአገር ግንባታ ሒደትን ለማጠናከርና ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር ዋልታና ማገር ሆነው ከሚያገለግሉት ግበዓቶች አንዱ ፍትሕን ማስፈን ነው፡፡

በአሸባሪነት የተሰየመን የመሰረዝ አንድምታዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ በሲመት ንግግራቸው ወቅት ከቀረቡት ጥሪ መካከል አንደኛው በተለያዩ አገሮች ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ሰላማዊ ትግል እንዲያደርጉ የሚለው ይገኝበታል፡፡ ለዚህ መነሻዎቹ የሕዝቡ ፍላጎት፣ የኢሕአዴግ ውሳኔ የጠቅላይ ሚኒስትሩም አጀንዳ የሆነው አገራዊ አንድነትን የማጠናከርና የዴሞክራሲ ሥርዓቱን የማስፋት ጉዳይን ተግባራዊ ማድረግ ናቸው፡፡

‹‹መሥራችና ባለቤት›› እና ‹‹መጤ›› ብሔረሰቦች ግንኙት ከሕገ መንግሥቱ አንፃር

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የአገራዊ ማንነትና የአገር ግንባታ ጉዳይ ለብዙዎች አጀንዳ እየሆነ መጥቷል፡፡ ጉባዔዎች እየተካሄዱ ነው፡፡ የተወሰኑ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ለእነዚህ ጉዳዮች ትኩረት ሰጥተው በመወያየትም ላይ ይገኛሉ፡፡ የተወሰኑ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ድርጅቶችም እነዚህን ውይይቶችና የራሳቸውንም ፕሮግራም በማዘጋጀት ለሕዝብ እያስተላለፉ ነው፡፡

በዘገየ ንግድ አየር ትራንስፖርት አገልግሎት የአጓጓዡ ኃላፊነት

በ1952 ዓ.ም. የወጣው የንግድ ሕግ ሥርዓት ካበጀላቸው ጉዳዮች መካከል የማጓጓዝና የማመላለስ ሥራ አንዱ ነው፡፡ የንግድ ሕጉ በሦስተኛው ክፍሉ ኢንሹራንስን ጨምሮ ለእነዚህ ጉዳይ ደንብ ሠርቷል፡፡ በባህር ላይ የሚደረግ የማጓጓዝ ተግባርን በሚመለከት የተለየና ራሱን የቻለ በዚሁ ዓመት የወጣ ሕግ አለ፡፡ የንግድ ሕጉ ትኩረት የሰጠባቸው በየብስና በአየር የሚደረጉ የማጓጓዝና የማመላለስ አገልግሎት ነው፡፡