Skip to main content
x

ኢትዮጵያ በንግድ ጦርነት ጦስ ሊጠቁ ከሚችሉ ቀዳሚ አገሮች ተርታ ተመደበች

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንግድና የልማት ጉባዔ (UNCATD) በዓለም ላይ እየታየ ያለውን የንግድና የታሪፍ ከለላ ዕርምጃ በተመለከተ በድረ ገጹ ባስነበበው ጽሑፍ፣ በወጪ ንግዳቸው ላይ ከፍተኛ ታሪፍ ሊጋጥማቸው ይችላሉ ካላቸው ከ30 በላይ አገሮች ውስጥ ኢትዮጵያን በሦስተኛ ደረጃ አስቀምጧል፡፡

ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የታክስ ወኪልነት የሙያ ሥራን የሚደነግግ መመርያ ሊተገብር ነው

ግብር ከፋዮች ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ጋር በታክስ አከፋፈልና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ በወኪሎቻቸው አማካይነት ከባለሥልጣኑ ጋር የሥራ ግንኙነት ማድረግ የሚያስችሉበት አሠራር ሊተገበር ዝግጅት መጀመሩ ይታወቃል፡፡

በሞጆ ከተማ በ100 ሚሊዮን ዶላር የቆዳ ኢንዱስትሪ ዞን ሊገነባ ነው

ከአዲስ አበባ ከተማ 76 ኪሎ ሜትር ርቀት በኦሮሚያ ክልል ሞጆ ከተማ አቅራቢያ በ100 ሚሊዮን ዶላር የቆዳ ኢንዱስትሪ ዞን ሊገነባ ነው፡፡ ለአካባቢያዊ ብክለት ከፍተኛ ድርሻ ያላቸውን የቆዳ ፋብሪካዎች አንድ ቦታ ለማሰባሰብ የታቀደው ከዓመታት በፊት ቢሆንም ዕቅዱ ተግባራዊ ሳይደረግ ቆይቷል፡፡ የኢትዮጵያ ቆዳና ቆዳ ውጤቶች ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዱ ለገሠ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የፕሮጀክቱ ጥናት ከሦስት ዓመት በፊት ቢጠናቀቅም ገንዘብ  ባለመገኘቱ ዘግይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ በአነስተኛ ወለድ ብድር በመፍቀዱ ወደ ሥራ እየተገባ ነው ብለዋል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ገዥ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፋይናንስ ጉዳዮች አማካሪ ሆኑ

ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥነት የተነሱት አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፋይናንስ ጉዳዮች ኃላፊ ሆኑ፡፡ ላለፉት 13 ዓመታት በገዥነት በቆዩት አቶ ተክለ ወልድ ምትክ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ሲሾሙ፣ አቶ በቃሉ ዘለቀ ደግሞ ምክትል ገዥ ሆነዋል፡፡ አቶ ተክለ ወልድ የተመደቡበት የፋይናንስ አማካሪነት ኃላፊነት ለመጀመርያ ጊዜ  ራሱን ችሎ መቋቋሙ ታውቋል፡፡

በውጭ ምንዛሪ አጠቃቀም ችግር ከገበያ እየወጡ ያሉ የንግድ ሰዎች የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይድረሱልን አሉ

በውጭ ምንዛሪ እጥረትና አጠቃቀም ችግር ምክንያት ጥሬ ዕቃ ማግኘት ባለመቻላቸው ከምርት እየወጡ መሆናቸውን የሚናገሩ የፋብሪካ ባለቤቶችና መድኃኒትን የመሳሰሉ አስፈላጊ ዕቃዎች የሚያስመጡ ነጋዴዎች፣ ከገበያ እየወጡ መሆኑን በመጥቀስ አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) እንዲደርሱላቸው ጠየቁ፡፡

ካስቴል የዘቢዳርን 40 በመቶ ድርሻ ለመግዛት ያቀረበውን ዋጋ ባለአክሲዮኖች አልተስማሙበትም

የዥማር ኩባንያ ባለአክሲዮኖች በዘቢዳር ቢራ ያላቸውን የ40 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ለካስቴል ግሩፕ (ቢጂአይ ኢትዮጵያ) ለመሸጥ ወሰኑ፡፡ ካስቴል ግሩፕ አክሲዮኖቻቸውን ለመግዛት ያቀረበላቸውን ዋጋ ግን እንደማይቀበሉ አስታወቁ፡፡ የዥማር ሁለገብ አክሲዮን ማኅበር አባላት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባካሄዱት ስብሰባ ወቅት፣ በዘቢዳር ቢራ ውስጥ ለያዙት የአክሲዮን ድርሻ የቀረበላቸው ዋጋ ከሚጠብቁት በታች በመሆኑ፣ የሽያጭ ዋጋው እንዲሻሻልና ለዚህም ቦርዱ ከካስቴል ግሩፕ ጋር እንዲደራደር ውክልና ሰጥተዋል፡፡

ለንግዱ ኅብረተሰብ በአንዴ የቀረቡት 21 ረቂቅ የታክስ መመርያዎች

የኢትዮጵያ ገቢዎች ጉምሩክ ባለሥልጣንና የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር፣ ባልተለመደ አኳኋን 21 ረቂቅ መመርያዎችን በማሰናዳት ከንግዱ ኅብረተሰብ ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡ ሰኔ 5 እና 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ውይይት ከተደረገባቸው ረቂቅ መመርያዎች መከካል 11ዱ በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በኩል የቀረቡ ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ረቂቅ መመርያዎችም በባለሥልጣኑ ለውይይት የቀረቡ ነበሩ፡፡

አንበሳ ጫማ በአፍሪካ አድናቆትን ካተረፉ ብራንዶች ተርታ በድጋሚ ሊመደብ ቻለ

ከተመሠረተ ከ80 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው አንበሳ ጫማ ፋብሪካ፣ በተጠቃሚዎች ምርጫ አማካይነት በሚሰጠው የብራንድ ደረጃ፣ ከአፍሪካ አድናቆትን ካተረፉ ትልልቅ ብራዶች ተርታ ዳግመኛ ውጤት ማግኘቱ ታወቀ፡፡