Skip to main content
x

ለሱሉልታ ከተማ የተቀናጀ የአካባቢ ልማት ፕሮጀክት ዕቅድ ቀረበ

የሁለት ዓመታት የጥናት ጊዜ የወሰደው የሱሉልታ ከተማ የተቀናጀ የአካባቢ ልማትና ክብካቤ ፕሮጀክቶች ንድፈ ሐሳብ ተጠናቆ ለውይይት ቀረበ፡፡ ኔስሌ ዋተርስ ኢትዮጵያ በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ የመጠጥ አምራች ኩባንያ ጠንሳሽነት የተጀመረው ይህ የተቀናጀ የአካባቢ ልማት ፕሮጀክት፣ ከከተማዋ አቀማመጥ እንዲሁም ከደረቅና ከፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሥራዎች ላይ ቅድሚያ በመስጠት አረንጓዴ የልማት ፕሮጀክቱ ጅማሮውን ያደርጋል ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ የዓለም የቡና ቅምሻ ውድድርን ታስተናግዳለች

ኢትዮጵያ እንድታስተናግደው የታጨችበት የዓለም የቡና ጥራት ውድድር ሲዘጋጅ ጥቂት ጊዜ አስቆጥሯል፡፡ ከአፍሪካ ብሩንዲና ሩዋንዳን ከዚህ ቀደም ያሳተፈው የቡና ጥራት ውድድር፣ ትልልቅ ቡና አምራች የሚባሉትን እነ ብራዚልና ኮሎምቢያን ጨምሮ ዘጠኝ የላቲን አሜሪካ አገሮችን ሲያሳትፍ ቆይቷል፡፡

ቱሪዝም ኢትዮጵያ ከመንግሥት በጀት ውጪ የራሱን የገቢ ምንጮች መጠቀም የሚችልበት የሕግ ማዕቀፍ ሊሰጠው ነው 

ቱሪዝም ኢትዮጵያ (የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት) በራሱ መንገድ ገቢ ማሰባሰብ የሚያስችለውን ረቂቅ ሕግ እንዳዘጋጀ አስታወቀ፡፡ በአዋጅ ቁጥር 1011/2011 እንደ አዲስ የተደራጀው ተቋሙ፣ የተሰጡትን ኃላፊነቶች በመንግሥት በጀት ብቻ ለመተግበር አዳጋች እንደሆበት በማስታወቁና ይህንኑ ችግሩን ለመንግሥት በማቅረብ የራሱን የገቢ ምንጭ በመፍጠር በጀት ማንቀሳቀስ እንደተፈቀደለት አስታውቋል፡፡

ግብርናው በመንግሥት ሐሳብና በባለሙያዎች ምልከታ መካከል

ከሚመስሉት ተቋማት ጋር ለዓመታት ሲጋባና ሲፋታ የኖረው የግብርና ሚኒስቴር፣ በዚህ ወር መጀመርያ ሳምንት የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸሙን ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ የሪፖርቱ የተወሰኑ ክፍሎች ላይ፣ በተለይ በወጪ ምርቶች ላይ የታየው የጥራትና የአኃዝ ችግር ከአንድ ሚኒስቴር የማይጠበቅ ቢሆንም በጥቅሉ ግን የዘርፉን ክንዋኔ በግርድፍ ለማሳየት ሞክሯል፡፡ 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ25 ቢሊዮን ዶላር ኩባንያ ለመሆን አቅዷል

በከፍተኛ ደረጃ ዕድገት እያስመዘገበ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ እ.ኤ.አ. በ2035፣ 25 ቢሊዮን ዶላር የሚወጣ ኩባንያ ለመሆን ማቀዱ ተሰማ፡፡ የአየር መንገዱ ማኔጅመንት የራዕይ 2025 ቀጣይ የሆነውን ራዕይ 2035 በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡

ለሰባት ኩባንያዎች የማዕድን ፍለጋ ፈቃድ ተሰጠ

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ለሰባት ኩባንያዎች ስምንት የማዕድን ፍለጋ ፈቃድ ሰጠ፡፡ ሚኒስቴሩ የፍለጋ ፈቃድ የሰጠው ለሰቆጣ የማዕድን ኃላፊነቱ የግል ማኅበር፣ ለአይጋ ትሬዲንግ ኢንዱስትሪስ፣ ለአጎዳዮ ሜታልስና ሌሎች ማድናት ኩባንያ፣ ለአፍሪካ ማይኒንግና ኢነርጂ፣ ለአልታው ሪሶርስስ ሊሚትድ፣ ለሰን ፒክ ኢትጵያና ለሒምራ ማይኒንግ ነው፡፡

በሴቶች ሠራተኞች አገልግሎት የሚሰጠው የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ሥራ ጀመረ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ75 ዓመታት በላይ በዘለቀው ዕድሜው በመላ አገሪቱ ከከፈታቸው ቅርንጫፎቹ በተለየ አገልግሎት ይሰጣል የተባለውን አንድ ቅርንጫፍ አዲስ አበባ ውስጥ ከፍቷል፡፡ የባንኩ 1,400ኛው ቅርንጫፍ በመሆን ለአገልግሎት የበቃው ይህ ቅርንጫፍ፣ የታዋቂውን የፋይናንስ ባለሙያ ስያሜ እንዲይዝም ተደርጓል፡፡

በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ሒደት የኢትዮጵያ ጉዞ

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት በሚተገበርበት ወቅት ያስገኛል ተብሎ ከሚጠበቀው ጠቀሜታ ጎን ለጎን አሉታዊ ተፅዕኖዎችም እንዳሉት እየተገለጸ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ይኼንን ስምምነት በተግባር ለመተርጎም በሕግ አፅድቃ መቀበሏንና ይህንኑ ሰነድም ለአፍሪካ ኅብረት ማስረከቧን ተከትሎ ከሚሰጡ አስተያየቶች መገንዘብ እንደሚቻለው፣ ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ጠቃሚ ነው የሚሉት አመዝነው ተገኝተዋል፡፡