Skip to main content
x

ምርት ገበያ በመጋቢት ወር የ3.6 ቢሊዮን ብር ግብይት አስተናገደ

በቅርቡ ወደ ማዕከላዊው የግብይት ሥርዓት የገባው አኩሪ አተር የግብይት መጠኑ ከዕለት ዕለት እየጨመረ መምጣቱንና በመጋቢት ወር የተካሄደው ግብይትም ካለፈው ወር ጋር ሲነጻጸር በመጠን የ46 በመቶ፣ በዋጋ የ47 በመቶ ጭማሪ እንደታየበት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አስታውቋል፡፡

የፈርኒቸር ቤተ ውበትና የግንባታ አጨራረስ ምርቶች ላይ ያተኮረ ዓውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው

የፈርኒቸር፣ ቤተ ውበትና ግንባታ አጨራረስ ምርቶችና አገልግሎቶች ላይ ያተኮረና ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰናዳ ዓውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው፡፡ የእነዚህ ምርቶችና አገልግሎቶች ዓውደ ርዕይና ጉባዔ በፕራና ኤቨንትስ ኩባንያና በሻክረክስ ንግድና ኤቨንት ማኔጅመንት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር አዘጋጅነት ከሚያዝያ 24 እስከ 26 ቀን 2011 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ ለማካሄድ የሚያስችሉ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል ተብሏል፡፡

የሞተር ዘይትና ቅባት እጥረት አሽከርካሪዎችን እያማረረ ነው

በአገሪቱ የተከሰተው የሞተር ዘይትና ቅባት እጥረት እንዳማረራቸው አሽከርካሪዎች ገለጹ፡፡ የሞተር ዘይትና ቅባት ከገበያ በመጥፋቱ ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን አሽከርካሪዎች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ አንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ዝቅተኛ የጥራት ደረጃ ያለው የሞተር ዘይት እንደሚሸጡ የተናገሩት አሽከርካሪዎች፣ በጥቁር ገበያ በከፍተኛ ዋጋ እየተሸጠ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

የውጭ  ምንዛሪ  ተመን  በገበያ  እንዲወሰን  መንግሥት  ማቀዱ ተሰማ

የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ የሚወሰንበት አሠራር ተግባራዊ እንዲሆን መንግሥት ዘላቂ ወይም የረዥም ጊዜ ዕቅድ መያዙ ተሰማ። አንድ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቁጥጥር ከሚደረግበት የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት እንዲያበቃ፣ በፍላጎትና አቅርቦት የገበያ መርህ የብር የውጭ ምንዛሪ ተመን እንዲወሰን መንግሥት አቅጣጫ አስቀምጧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ አዳዲስ የቦርድ አባላት ሾሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብን በተመለከቱ ጉዳዮችና በዚሁ ዘርፍ ቁጥጥር ለማድረግ ሥልጣን ለተሰጠው የኢትዮጵያ ሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፣ አዲስ ቦርድ ሰብሳቢና የቦርድ አባላትን ሰየሙ፡፡

ለሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ አዲስ የቦርድ አባላት ተሾሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ አዲስ ሰብሳቢና አባላት ሰየሙ፡፡ በዚሁ አዲስ ምደባ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነዋል፡፡ ከቦርድ ሰብሳቢው በተጨማሪ የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የቦርድ አባላት እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመደቡት አቶ መንግሥቱ ዱቢቾ፣ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ አቶ እሸቱ አስፋው፣ አቶ ጥሩነህ ሚጣፋ፣ አቶ ገለታ ሥዩም፣ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)፣ አቶ ስንታየሁ ደምሴ፣  አቶ ደመላሽ ጌታቸው፣ አቶ ቢርቢርሳ ደምሴ፣ አቶ መላኩ እዘዘው (ኢንጂነር) እና አቶ ጌታቸው ረጋሳ ናቸው፡፡

ንግድ ባንክ የኦሮሚያ ባንክ ኃላፊን በምክትል ፕሬዚዳንትነት ሾመ

በወለድ አልባ የባንክ አገልግሎት ፈር ቀዳጅ በመሆን በመስኩ ከተቀሩት ባንኮች ሰፊውን የገበያ ድርሻ የያዘው የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ሲሆን፣ ይህንን አገልግሎት በዳይሬክተርነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ኑሪ ሁሴን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሰየሙ፡፡

የዘቢዳር ቢራ ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች ካስትል ኩባንያ ባቀረበው የዋጋ ጭማሪ ከስምምነት አልደረሱም

የዘቢዳር ቢራ አክሲዮን ማኅበር የ40 በመቶ ባለድርሻ የሆነው ዥማር ሁለገብ አክሲዮን ማኅበር አባላት አክሲዮናቸውን እንዲሸጡ ከካስትል ኩባንያ ጋር ሲደረግ የነበረው ድርድር የመሸጫ ዋጋ ጭማሪ ቢያሳይም፣ ባለአክሲዮኖች ግን በጭማሪው ላይ ስምምነት ባለማሳየታቸው ድምፅ እንዲሰጡበት ተደረገ፡፡