Skip to main content
x

በአገሪቱ ‹‹የጨለማ ኢኮኖሚ›› እንቅስቃሴ መንሰራፋቱን የገቢዎች ሚኒስትሯ አመለከቱ

ሕግና ሥርዓትን ተከትሎ ከሚደረገው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በተቃራኒው ሰፊ የሆነ ‹‹የጨለማ ኢኮኖሚ›› እንቅስቃሴ መኖሩንና ሁሉም የመንግሥት መዋቅር ተናቦና ተቀናጅቶ መዋቅሩን ካላፈራረሰው፣ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት ከማድረስ አልፎ ፖለቲካዊ አንድምታ ሊኖረው እንደሚችል የገቢዎች ሚኒስትሯ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡

በተጓተቱ የመንግሥት ፕሮጀክቶች ሳቢያ ከ43 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ አጋጥሟል ተባለ

ገንዘብ ሚኒስቴር በግማሽ ዓመቱ የታየውን የበጀት አፈጻጸም በማስልከት ማክሰኞ፣ ጥር 28 ቀን 2011 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ፣ ከ102 መሥሪያ ቤቶች የ1,000 ፕሮጀክቶችን ዝርዝር ሒደት የሚያሳይ መግለጫ ወይም ፕሮፋይል ተሰናድቶ ከአንድ እስከ ሰባት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ የተጓተቱ ፕሮጀክቶች የ43.1 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ ማስከተላቸውን አስታወቀ፡፡

የኢትዮ ቴሌኮምን ሞኖፖል ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ተላከ

ለዓመታት በመንግሥት በሞኖፖል ተይዞ የቆየው የቴሌኮም ዘርፍ ለውድድር ክፍት እንደሚደረግ፣ ይህንንም የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ለተወካዮች ምክር ቤት ተላከ፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም የገበያ የበላይነትንና የሞኖፖል ድርሻን የሚያስቀር የገበያ ሥርዓት እንደሚፈጠር መንግሥት አስታውቋል፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የንግድ ቤቶችን የኪራይ ውል ቀነ ገደብ አራዘመ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በሚያከራያቸው ንግድ ቤቶች ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ካደረገ በኋላ፣ ደንበኞች አዲስ ውል እንዲገቡ ባስቀመጠው ቀነ ገደብ በርካታ ደንበኞች በብዛት በመምጣታቸውና መጨናነቅ በመፈጠሩ ቀነ ገደቡን አራዘመ፡፡

ንግድ ባንኮች ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ አስመዘገቡ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ የሁሉም ንግድ ባንኮች የ2011 ዓ.ም. ግማሽ ዓመት አፈጻጸም ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ወቅት ካስመዘገቡት ውጤት ይልቅ የበለጠ መሆኑ ተመለከተ፡፡ 17ቱ ባንኮች በስድስት ወራት ብቻ ከታክስና ከሌሎች ተቀናሾች በፊት ከ16.4 ቢሊዮን ብር አስመዝግበዋል፡፡

የመንግሥትና የግሉን ዘርፍ የምክክር መድረክ ዳግም ለማስጀመር ታስቧል

ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (አይኤፍሲ)፣ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል ፖሊሲ ነክ፣ የማክሮ ኢኮኖሚና ሌሎችም በንግዱ ማኅበረሰብ ዘንድ ማነቆ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሁሉ መነጋገሪያና መፍትሔ ማመላከቻ የሚሆን የጋራ የውይይት መድረክ ዳግም እንዲጀመር እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡