Skip to main content
x

በሪል ስቴት ዘርፍ በተካሄደ ዳሰሳ ጥናት በወረቀትና በተግባር ባለው እውነታ ከፍተኛ ልዩነት መኖሩ ይፋ ሆነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) በሪል ስቴት ዘርፍ የተንሰራፉ ችግሮችን እንዲፈታ ከሁለት ሳምንት በፊት ያቋቋሙት ግብረ ኃይል ባካሄደው መጠነኛ ዳሰሳ፣ በማኅደር በሠፈረውና ተግባራዊ በሆነው ግንባታ መካከል ከፍተኛ ልዩነት እንዳለ አመለከተ፡፡

ሪል ስቴት ኩባንያዎች ያለባቸውን ውዝፍ ዕዳ እንዲከፍሉ ተጠየቀ

በቅርቡ በከተማ ደረጃ የታክስ ንቅናቄ የጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የሪል ስቴት ኩባንያዎች ያለባቸውን ውዝፍ ዕዳ እንዲከፍሉ ጠየቀ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 130 የሪል ስቴት ኩባንያዎች የሚገኙ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ባካሄደው ጥናት ስድስት ሪል ስቴት ኩባንያዎች ብቻ በአግባቡ የቤት ግብር መክፈላቸውን ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ አስተዳደር ከ7,700 በላይ ለሚሆኑ ነጋዴዎች የግብር ዕዳ ምሕረት ማድረጉን አስታወቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ የተጣለባቸው ግብር ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ እንዲታይላቸው ሲጠይቁ ለቆዩ 6,000 ነጋዴዎች፣ እንዲሁም በግብር ይግባኝ ተከራክረው ለተፈረደባቸው 1,780 ነጋዴዎችም ምሕረት እንዲደረግላቸው ካቢኔያቸው መወሰኑን አስታወቁ።

በማስፋፊያ የታጀበው የሞጆ ተርሚናል የወደብነት ጉዞ

በሙሉ አቅሙ በ2004 ዓ.ም. ሥራ የጀመረው የሞጆ ደረቅ ወደብ፣ ሰሞኑን ከተገዙት 13 የኮንቴይነር መጫኛና ማውረጃ ማሽኖች እንዲሁም ኮንቴይነርን ጨምሮ በብትን የመጡ ዕቃዎችን  የሚጭኑ፣ የሚያወርዱና በ150 ሚሊዮን ዶላር ከተገዙ 28 ፎርክሊፍቶች ውስጥ አብዛኛውን ተረክቧል፡፡

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ለኤክስፖርተሮች ከ7.4 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ሰጠ

​​​​​​​የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ለላኪዎችና ለወጪ ንግድ ምርት አምራቾች ከ7.4 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ሰጠ፡፡ ይህ የተገለጸው ባንኩ የወጪ ንግድ ዘርፍ ለተሰማሩ የባንኩ ደንበኞች ዕውቅና በሰጠበት ፕሮግራም ላይ ነው፡፡

የፍጥነት መንገዱ ገቢ በእጥፍ መጨመሩ ተገለጸ

​​​​​​​በአገሪቱ የመጀመርያው የፍጥነት መንገድ በመሆን ከአራት ዓመት በፊት ሥራ የጀመረው የአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ ዕለታዊ የተሽከርካሪዎች ፍሰት እያደገ በመሄዱ ገቢው እየጨመረ መምጣቱ ተመለከተ፡፡ አማካይ ዕለታዊ ገቢው በእጥፍ መጨመሩም ታውቋል፡፡

ለቢራ ማስታወቂያ ሰዓት እላፊ

የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያዎችን የሚገድብ ረቂቅ አዋጅ ለማፅደቅ የተደረገው ውይይት አግራሞት ከፈጠረባቸው አንዱ ነኝ፡፡ ሕጉ እንዲፀድቅ የሚደረገው ሙግት  ከሌሎች አዋጆች በተለየ እንዲታይ ያደርገዋል ማለት ይቻላል፡፡

ከ10 ሺሕ በላይ ሥራ ፈጣሪ ሴቶችን ያካተተው ፕሮጀክት

የሴቶች ኢንተርፕሩነርሺፕ ልማት ፕሮጀክት በፌዴራል ከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ሥር ከሚገኙ ፕሮግራሞች አንዱ ነው፡፡ የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማስፋት ሲባል መንግሥት ከዓለም ባንክ ጋር በጋራ የሚተገብረው ፕሮጀክት ነው፡፡ ለተግባራዊነቱም ዓለም ባንክ 50 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ ለመንግሥት አበድሯል፡፡ ሦስት ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ለሥራ ማስኬጃና ለተያያዥ ጉዳዮች በስጦታ የቀረበ ነው፡፡