Skip to main content
x

የኤርትራ ወደቦችን ለመጠቀም ዝግጅት መደረጉ ተመለከተ

ከሁለት አሥርት ዓመታት በኋላ የኤርትራ ወደቦችን እንደ አዲስ ለመጠቀም እየተካሄደ ባለው ዝግጅት፣ አገራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ ዕቅድ መዘጋጀቱ ተመለከተ፡፡ የኤርትራ ወደቦች የሆኑትን አሰብና ምፅዋ ለመጠቀም የሚያስችል ዝግጅት እንዲያካሂድ ኃላፊነት የተሰጠው፣ ከዘርፍ መሥሪያ ቤቶች የተውጣጣ የቴክኒክ ኮሚቴና በከፍተኛ ባለሥልጣናት የተቋቋመው ዓብይ ኮሚቴ በቂ ዝግጅት ማድረጉ ተገልጿል፡፡

የሩዝ ፈንዲሻ የተዋወቀበት የምርምር ማዕከል የወደፊት ስንቆች

በጃፓኖች ድጋፍ ከሦስት ዓመታት የግንባታ ሥራ በኋላ ለአገልግሎት የበቃው ብሔራዊ የሩዝ ምርምርና ሥልጠና ማዕከል፣ በኢትዮጵያ ለሩዝ እርሻ ተስማሚ የሆኑ አካባቢዎችን በማዳረስ የምግብ አቅርቦትን የማሻሻል ስንቅ የተቋጠረበት ትልም ይዟል፡፡

አዲስ ባንክ ከ113 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፉን ለካፒታል ማሳደጊያነት እንዲውል ወሰነ

ከ16ቱ የግል ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ፣  በፋይናንስ ኢንዱስትሪው ውስጥ መንቀሳቀስ ከጀመረ ስድስት ዓመታት አስቆጥሯል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ባንኮችን ለማቋቋም የሚያስፈልገው ዝቅተኛ የተከፈለ ካፒታል 500 ሚሊዮን ብር መሆን እንዳለበት ከመደንገጉ ቀደም ብሎ ሲተገበር በቆየው መመርያ መሠረት በ100 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ከተቋቋሙት የመጨረሻዎቹ ሦስት ባንኮች አንዱ መሆኑ ይታወሳል፡፡

የእናት ባንክ መሥራቿ መዓዛ ሽኝት

የእናት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ የነበሩትና ከሁለት ሳምንት በፊት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በመሆን የተሾሙት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ፣ በእናት ባንክ ለነበራቸው ቆይታ ዕውቅና ለመስጠትና ለአዲሱ ሹመታቸውም የባንኩ ማኅበረሰብ የእንኳን ደስ አለዎ ምኞቱን ለመግለጽ፣ ሐሙስ ኅዳር 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ምሽት በኢሊሊ ሆቴል ግብዣ ተሰናድቶ ነበር፡፡

ከሩብ ትሪሊዮን ብር በላይ የንግድ ሚዛን ጉድለት የሚታይበትን የወጪ ንግድ ዘርፍ የመታደግ ጅምር

‹‹ፋይናንስ ለአገራዊና ለወጪ ንግድ ዕድገት፣›› በሚል ርዕስ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ኮንፈረንስ ወቅት የወጪ ንግዱን የተመለከተ ጽሑፍ መወያያ ከነበሩ ጉዳዮች አንዱ ነበር፡፡

የመንግሥት የዲጂታል ግዥ መተግበሪያ ሥርዓት ይፋ ሆነ

የመንግሥት ተቋማትን ልማዳዊ የግዥ ሥርዓት በኤሌክትሮኒክ የታገዘ ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል የስትራቴጂ ዕግድና መተግበሪያ ይፋ ሆነ፡፡ ሐሙስ፣ ኅዳር 6 ቀን 2011 ዓ.ም. በገንዘብ ሚኒስቴር በተካሄደ ዓውደ ጥናት የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ ከኢንፎርሜሽንና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር ጋር በመሆን የተዘጋጀውን የኤሌክትሮኒክ ግዥ ስትራቴጂ ከዕቅድ መተግበሪያ ሥርዓት ጋር አጣምረው ይፋ አድርገዋል፡፡

ወጋገን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በማትረፍ ሦስተኛው የግል ባንክ ሆነ

ከሃያ ዓመታት በላይ ካስቆጠሩ የግል ባንኮች ውስጥ አንዱ የሆነው ወጋገን ባንክ፣ ከታክስ በፊት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በማትረፍ የ2010 ዓ.ም. ሒሳቡን ዘግቷል፡፡ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ካተረፉ ሦስት የግል ባንኮችም አንዱ ለመሆን በቅቷል፡፡  

ኢትዮጵያ የልማታዊ መንግሥት መንገዷን እየቀየረች ስለመሆኗ የዓለም ባንክ ገለጸ

የዓለም ባንክ ላለፉት 15 ዓመታት ተቋርጦ የቆየውን የቀጥታ በጀት ድጋፍ እንደ አዲስ በማስጀመር ለኢትዮጵያ የ1.2 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አስተዳደር እየወሳዳቸው የሚገኙ ‹‹መዋቅራዊ የለውጥ ሒደቶች›› ላይ እምነት እንዳለውና እንደ ቴሌኮም፣ ሎጂስቲክስና የመሳሰሉትን ለግሉ ዘርፍ ክፍት የማድረጉ ዕርምጃም እንደሚደገፍ አስታውቋል፡፡