Skip to main content
x

አዳዲስ ቤቶችን ለመገንባት የተዘጋጀው ቤቶች ኮርፖሬሽን በንግድ ቤቶች ላይ የሚፈጸም ሕገወጥነትን አልታገስም አለ

ከ27 ዓመታት በኋላ እንደ አዲስ ወደ ቤቶች ግንባታ ለመግባት እየተንደረደረ የሚገኘው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ በሚያስተዳድራቸው የንግድ ቤቶች ላይ የተንሰራፋውን ሕገወጥነት እንደሚገታ አስታወቀ፡፡

በ200 ሚሊዮን ብር የተቋቋመው ብሔራዊ የሩዝ ምርምር ማዕከል ተመረቀ

በጃፓን መንግሥት የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ በ200 ሚሊዮን ብር ወጪ በአማራ ክልል የተገነባው ብሔራዊ የሩዝ ምርምርና ሥልጠና ማዕከል ተመረቀ፡፡ ፎገራ ብሔራዊ የሩዝ ምርምርና ሥልጠና ማዕከል፣ በአገሪቱ ለሩዝ እርሻ ተስማሚነቱ ለሚነገርለት 30 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ለማልማት ብሎም ከውጭ ለሚገባውና ከ300 ሺሕ ቶን በላይ ከውጭ የሚገባ ሩዝ ምርትን ለመተካት ተስፋ የተጣለበት ብሔራዊ የሩዝ ማዕከል የአገሪቱ 18ኛው የግብርና ምርምር ማዕከል ሆኖ ሐሙስ፣ ኅዳር 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ተመርቋል።

አቢሲንያ ባንክ በአዲሱ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት ሳቢያ ትርፉ መቀነሱን ገለጸ

ከሰሞኑ የፋይናንስ ተቋማት የ2010 ዓ.ም. አፈጻጸማቸውን የሚያመላክቱ ሪፖርቶችን ለአክሲዮን ባለድርሻዎች ይፋ እያደረጉ ነው፡፡ ከእነዚህ መካከልም ቅዳሜ፣ ኅዳር 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ዓመታዊ ሪፖርቱን ይፋ ያደረገው አቢሲኒያ ባንክ እንዳስታወቀው በ2009 ዓ.ም.

በኢትዮጵያውያን የተቋቋመው የሞባይልና የኮምፒዩተር መገጣጠሚያ በ50 ሚሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ሥራ ጀመረ  

አይፕሮ ኢትዮጵያ የተሰኘው የሞባይል፣ የኮምፒዩተርና መለዋወጫዎች መገጣጠሚያ ፋብሪካ ከውጭ በመጡ ባለሀብት በ50 ሚሊዮን ብር ካፒታል ተገንብቶ ሥራውን በቅርቡ ጀምሯል፡፡ ይህንኑ በማስመልከትም በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በደሴ ከተማ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ፋብሪካው በይፋ ወደ ምርት ተግባር መግባቱ ተበስሯል፡፡

ብርሃን ባንክ መጠነኛ የትርፍ ቅናሽ ባስመዘገበበት ዓመት የተስፋፋ የባንክ እንቅስቃሴ እንደነበረው አስታወቀ

በአገሪቱ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ መንቀሳቀስ ከጀመረ ስድስት ዓመታት ያስቆጠረው ብርሃን ባንክ፣ ከ16 የግል ባንኮች ውስጥ በተለየ የሚታይበት ገጽታ ተላብሷል፡፡ ይኸውም 15 ሺሕ ገደማ ባለአክሲዮኖችን በመያዝ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ከአገሪቱ ባንኮች መካከል በርካታ ባለአክሲዮኖችን በመያዝ ቀዳሚ ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡

ቤቶች ኮርፖሬሽን በሚያከራያቸው ንግድ ቤቶች ላይ የዋጋ ማሻሻያ አደረገ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከስምንት ዓመት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ  በሚያከራያቸው ንግድ ቤቶች ላይ የኪራይ ተመን ጭማሪ አደረገ፡፡ ኮርፖሬሽኑ የኪራይ ተመን ማሻሻያ ያደረገባቸው አሥር ዋና ዋና ምክንያቶችን በመያዝ፣ ማክሰኞ ኅዳር 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ከደንበኞቹ ጋር በካፒታል ሆቴል መክሯል፡፡

የግሉን ዘርፍ በቤቶች ግንባታ በስፋት የሚያሳትፍ ረቂቅ ሰነድ ተዘጋጀ

በመኖሪያ ቤቶች ግንባታ በከፍተኛ ደረጃ እየተፈተነ ያለው መንግሥት፣ በመጨረሻ የግሉን ዘርፍ በስፋት ካላሳተፈ ችግሩን እንደማይፈታው አመነ፡፡ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በግልና በመንግሥት አጋርነት አሠራር፣ የውጭና የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮችን ማሳተፍ የሚያስችል ሰነድ አዘጋጅቷል፡፡

ምክትል ከንቲባው የራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቀጥል የመፍትሔ አማራጭ አስቀመጡ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ከራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ከወ/ሪት ሳምራዊት ፍቅሩ ጋር በመወያየት፣ ራይድ የጀመረው ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠናክሮ መቀጠል በሚችልበት አማራጭ መፍትሔ ዙሪያ መከሩ።