Skip to main content
x

አቢሲኒያ ባንክ ሒሳቤን በአይኤፍአርኤስ መሥራቴ ትርፌን ቀነሰው አለ

በአዲሱ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃ (አይኤፍአርኤስ/IFRS) በመጠቀም ዓመታዊ ሒሳቡን የሠራው አቢሲኒያ ባንክ የ2010 የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 765.7 ሚሊዮን ብር ማትረፍ መቻሉንና አስታወቀ፡፡ ይህ ትርፍ በቀድሞው የሒሳብ ሪፖርት አሠራር ቢሆን 857.5 ሚሊዮን ብር ይሆን እንደነበር አስታውቋል፡፡

ምርት ገበያው በጥቅምት ወር ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው ቡና አገበያየ

በተጠናቀቀው የጥቅምት ወር በኢትዮጵያ የምርት ገበያ የቡና ግብይት መጠን ከቀዳሚው ወር በ74 በመቶ ጭማሪ የታየበት ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ የምርት ገበያ የጥቅምት ወር ግብይቱን በተመለከተ ያጠናከረው መረጃ እንደሚያሳየው፣ በቡና ግብይት ዋጋ በ76 በመቶ ጨምሮ 1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው የቡና ግብይት ተፈጽሟል፡፡

የትራንስፖርት አሠሪዎች ፌዴሬሽን ተመሠረተ

ለዓመታት በውጣ ውረዶች የተፈተነው የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሠሪዎች ፌዴሬሽን ምሥረታ ተከናወነ፡፡ ሥራ መጀመሩም ተገልጿል፡፡   ፌዴሬሽኑ በይፋ ሥራ መጀመሩን ለማሳወቅ  ቅዳሜ ጥቅምት 24 ቀን 2011 ዓ.ም. በተሰናዳው ፕሮግራም ወቅት እንደተገለጸው፣ በትራንስፖርት ዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ከዚህ ቀደም በተለያዩ መንገዶች ማኅበር ለመመሥረት ያደረጉት ጥረት ሳይሳካላቸው ቢቆይም፣ በአሁኑ ወቅት ተሳክቶላቸው የዘርፉን የአሠሪዎች ማኅበር ዕውን አድርገዋል፡፡

ዓባይ ባንክ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ ቢያስመዘግብም ዓለም አቀፍ ባንኮች የወጣባቸው ሕግ ጫና እንዳሳደረበት ገለጸ

ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ የተከሰው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ብሎም በዓለም የነበረው ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ የባንክ ኢንዱስትሪው ላይ ጫና ማሳረፋቸው ሲገለጽ ቢቆይም፣ ዓባይ ባንክ እንደሌሎቹ ባንኮች ሁሉ የተሻለ ውጤት ያስመዘገበበት ዓመት እንደነበር አስታውቋል፡፡

የቀላል ባቡር ፕሮጀክትን ለመጠገን 70 ሚሊዮን ብር ይጠይቃል ተባለ

ሥራ በጀመረባቸው ሦስት ዓመታት ውስጥ ተደጋጋሚ ብልሽቶች እያጋጠሙት በየመንገዱ ባቡሮቹ የሚቆሙት የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት መስመር፣ በተለይም የኤሌክትሪክ ኬብሎቹ ላይ ባጋጠሙት ብልሽቶች ሳቢያና በሌሎችም ጥገናዎች ምክንያት እስከ 70 ሚሊዮን ብር የሚገመት ወጪ ሊያወጣ እንደሚችል ተገለጸ፡፡

በሐሰተኛ ደረሰኝ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት ፈጽመዋል የተባሉ 124 ድርጅቶች እየተመረመሩ ነው

በቅርቡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱ ካቢኔ አባል ሆኖ የተዋቀረው የገቢዎች ሚኒስቴር፣ ሕገወጥና ሐሰተኛ ደረሰኞችን ሲሸጡ የነበሩና በሐሰተኛ ሰነዶች ሲያጭበረብሩ የቆዩ 124 ድርጅቶችና ግለሰቦችን ዝርዝር ይፋ በማድረግ፣ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ሕገወጥ ግብይት በመፈጸማቸው የወንጀል ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኙ አስታወቀ፡፡

ሐሰተኛ ደረሰኝ አትመው በመሸጥ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት የፈጸሙ 124 ድርጅቶች ይፋ ተደረጉ

ትክክለኛ ማንነታቸውና አድራሻቸውን ሆነ ብለው በሐሰተኛ ሰነዶች በመሰወርና ደረሰኝ አትመው በመሸጥ ተግባር እጅ ከፍንጅ የተያዙትን ጨምሮ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት ሲፈጽሙ የነበሩ 124 ሐሰተኛ ድርጅቶች መያዛቸውን አዲሱ የገቢዎች ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።

የትራንስፖርት ባለሥልጣንና በቴክኖሎጂ አገልግሎት በሚያቀርቡ ድርጅቶች መካከል ውዝግቡ ቀጥሏል

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ሰሞኑን በንግድ አገልግሎት ዘርፍ በተለይም በኪራይ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጡ ካስታወቁና በጥሪና በአፕልኬሽን በመጠቀም በቴክኖሎጂ ትራንስፖርት ዘርፉን በሚያግዙ ተቋማት ላይ ዘመቻ ከፍቷል፡፡