Skip to main content
x

የአቪዬሽን ገበያ ለመክፈት የቀረበው ረቂቅ ሕግ ተቃውሞ ገጠመው

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የአገር ውስጥ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪን ለማሳደግ ያረቀቀው የአቪዬሽን ሕግ፣ ከባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው፡፡ ባለሥልጣኑ መንግሥት እየተገበረ ካለው የኢኮኖሚ ለውጥ ጋር የሚሄድና የአገሪቱን የአቪዬሽን ዘርፍ ለማሳደግ ይረዳሉ ያላቸውን፣ የኤርፖርቶች ግንባታና አስተዳደር አዋጅና የአየር ትራንስፖርት ማስፋፊያ ደንብ አዘጋጅቶ ለውይይት አቅርቧል፡፡

በኤጀንሲዎች ለባንኮች ጥበቃ ሥራ የሚመደቡ ሠራተኞች የ70 በመቶ ክፍያ እንዲያገኙ ሊደረግ ነው  

አሠሪዎችንና ሠራተኞችን በማገናኘት የሥራ መስክ ሠራተኞችን እየመለመሉ ለተቋማት የሚያቀርቡ ኤጀንሲዎች ለሚያስቀጥሯቸው ሠራተኞች የሚከፍሉት ገንዘብ በርካታ ተቃውሞ ሲቀርብበት ቆይቷል፡፡ የጉልበት ብዝበዛ እያካሄዱ ነው በማለት በርካቶች ክፉኛ ሲተቿቸው ሰንብተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መርከብ ከቻይና ወደ ሴኔጋል ጭነት ማጓጓዝ ጀመረች

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ መርከቦች የኤርትራ ጭነቶችን ወደ ቻይና በማጓጓዝ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፡፡ ሰሞኑንም ሰመራ የተሰኘችው የኢትዮጵያ መርከብ ለመጀመርያ ጊዜ ከቻይና ያጓጓዘቻቸውን ጭነቶች ወደ ሴኔጋል ማድረሷን የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል፡፡

ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ዘርፍ ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት ሊሳተፍ ነው

ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (አይኤፍሲ) ከኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ጋር በመተባበር ለዘርፉ ፍኖተ ካርታ ከማዘጋጀት ጀምሮ፣ የአቅም ግንባታ ድጋፎችንና የቱሪስት መዳረሻዎችን በማልማት ዘርፉ የሚያድግበትን የማማከር ድጋፍ ለመስጠት ስምምነት ፈረመ፡፡

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ በ10ኛ ዓመቱ

በባንክ ኢንዱስትሪው አሥራ ሦስተኛ በመሆን ሥራ የጀመረው ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ የአሥረኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን እየዘከረ ነው፡፡ የምሥረታ በዓሉን በማስመልከት ሐሙስ፣ የካቲት 21 ቀን 2011 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ባንኩን ለማቋቋም ተሰባስበው የነበሩ ጥቂት አደራጆች እንቅስቃሴ የጀመሩት ከ12 ዓመታት በፊት ነበር፡፡

የመጠጥ አምራቾች ማኅበር እሽግ መጠጦች አንገት ክዳን ሽፋን ለማንሳት ተስማሙ

ከስድስት ወራት በፊት ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ፈቃድ አግኝቶ የተቋቋመው የኢትዮጵያ የታሸገ ውኃና የለስላሳ መጠጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማኅበር ለአካባቢ ብክለት መንስዔ የሆነውን የመጠጦች አንገት ላይ የሚታሸገውን የፕላስቲክ ሽፋን ለማንሳት ወሰነ፡፡

ለሦስት ነባር የባንክ ባለሙያዎች ዕውቅና ተሰጠ

የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉና፣ ከግል ባንኮችም ትልልቆቹን ሦስት ባንኮች በፕሬዚዳንትነት ለመሩ ባለሙያዎች ዕውቅና ሰጠ። በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምሥጋና በማቅረብ፣ ማኅበሩ ዕውቅና የሰጣቸው ለአቢሲኒያ፣ ለወጋገንና ለንብ ባንኮች የቀድሞ ፕሬዚዳንቶች ናቸው።

በውጭ የሚኖሩ ዜጎች በአገር ቤት ለዘመዶቻቸው የሕክምና ሽፋን መግዛት የሚችሉበት አሠራር ተዘረጋ

ከኢትዮጵያ ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በርካታ በመሆኑ ጭምር ባንኮች ከዳያስፖራው ጋር የተገናኙ አዳዲስ አገልግሎቶች ስለመጀመራቸው እያስተዋወቁ ነው፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳያስፖራ የቤት መገንቢያ ብድር በማመቻቸት ሥራ መጀመሩ በምሳሌነት ሊጠቀስ ይችላል፡፡

የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ለሦስት ባለሙያዎች የዕውቅና ሽልማት ሰጠ

የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ለበርካታ ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩና ከ16 የግል ባንኮች ውስጥ ትልልቅ የሚባሉትን ሦስት የግል ባንኮች በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ ለነበሩ ባለሙያዎች ዕውቅና ሰጠ፡፡