Skip to main content
x

በስም የቀረው የእንስሳት ሀብት

ኢትዮጵያ ያሏትን ኢኮኖሚያዊ ሀብቶች በአግባቡ መጠቀም ካለመቻሏም ባሻገር፣ ሀብቶቿን ለሕዝብ ጥቅም እንዲውሉ ለማድረግ የሚያስችሉ ፖሊሲዎች እየተቀረፁ በአግባቡ አለመተግበራቸውም ከአገሪቱ ችግሮች ውስጥ ይመደባል፡፡

ከወራት በፊት ከተመረቀው የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምርቶች ለውጭ ገበያ መቅረብ ጀመሩ

ከወራት በፊት የተመረቀው የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በአሥር ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው በጨርቃ ጨርቅ አምራችነቱ የሚታወቀውና አንቴክስ የተባለው የቻይና ኩባንያ፣ የሙከራ ሥራውን አጠናቆ የመጀመርያ ምርቱን ለውጭ ገበያ አቀረበ፡፡

የውጭ ምንዛሪ ከአገር የማሸሽ ድርጊት ሊቆም ባለመቻሉ ትክክለኛ ምንጩን ለማወቅ ባንኮች ሊፈተሹ እንደሚገባ ተጠቆመ

በአገር ውስጥ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ባለበት ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪና የኢትዮጵያ የመገበያያ ብርን ከአገር የማሸሽ የወንጀል ድርጊት በየዕለቱ ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን፣ ትኩረት ተሰጥቶት ችግሩን ከምንጩ ለይቶ መግታት ካልተቻለ ውጤቱ አሳሳቢ እንደሚሆን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ። ለዚህም የባንኮችን አሠራር መፈተሽ አስፈላጊ ነው ተብሏል፡፡

የሪል ስቴት ኩባንያዎች መረጃ እንዲልኩ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ጠየቀ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ከተማ በሪል ስቴት ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች፣ የገነቧቸውንና የሚገነቧቸውን ቤቶች መረጃ እንዲልኩለት ጠየቀ፡፡ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ ትልልቅ ሪል ስቴት ኩባንያዎች ታኅሳስ 15 ቀን 2011 ዓ.ም.

በስንክ ሳር የተተበተበው የወጪ ንግድ

የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ በ2007 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ አሥር ቢሊዮን ዶላር ያስገኛል ተብሎ በዕቅድ ተይዞ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይህ ዕቅድ ከአፈጻጸሙ አንፃር ሲመዘን እጅግ ሰፊ ልዩነት በማሳየቱ በዕቅድ የተያዘውን ያህል ማሳካት ሳይቻል ቀርቷል፡፡

በመንታ መንገድ ላይ የሚገኘው የሪል ስቴት ልማት

ኢሕአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረበት 1983 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 1996 ዓ.ም. ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ የሪል ስቴት ልማት ብዙም አይታወቅም ነበር፡፡ በእርግጥ በ1990ዎቹ መጀመርያ አያት መኖሪያ ቤቶች፣ ሰንሻይን ኮንስትራክሽን፣ ጃክሮስና ሀቢታት ኒው ፍላዎር በተወሰነ ደረጃ ፈር ቀዳጅ በመሆን ግንባታ ጀምረው ነበር፡፡

የሚጠበቅበትን ያህል እየጠቀመ ያልሆነው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት

የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለአገር ውስጥ ቴክኖሎጂ ሽግግር ያበረከተውን አስተዋጽኦ በተመለከተ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ሰሞኑን አንድ የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የአገሪቱን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴንና እየሰጠ ያለውን ጥቅም አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት፣ በኢንቨስትመንት ኮሚሽን የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ድጋፍ ዳይሬክተር አቶ ስንታየሁ መንግሥቴ ናቸው፡፡

እናት ባንክ ከምርት ገበያው ጋር ለመሥራት 16ኛ ባንክ ሆነ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አብረውት የሚሠሩትን ባንኮች ቁጥር 16 ማድረሱን አስታወቀ፡፡ ምርት ገበያው ባለፈው ሐሙስ ታኅሳስ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ከእናት ባንክ ጋር ባደረገው ስምምነት ላይ እንደተገለጸው፣ እናት ባንክ ከምርት ገበያው ጋር በመሥራት 16ኛው ባንክ በመሆን ዘመናዊ የግብይት ሥርዓቱን ተቀላቅሏል፡፡

ሲቪል አቪዬሽን የግሉን ዘርፍ ያበረታታል ያለውን ሕግ እያረቀቀ ነው

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የግሉ ዘርፍ በአቪዬሽን መስክ ኢንቨስት እንዲያደርግ የሚያበረታታ ሕግና ደንብ በማርቀቅ ላይ ነው፡፡ ባለሥልጣኑ ዓርብ ታኅሳስ 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ከባለድርሻ አካላት ጋር ባካሄደው የምክክር መድረክ ያዘጋጀውን ረቂቅ የሲቪል አቪዬሽን አዋጅ ማሻሻያ፣ የአየር ትራንስፖርት ተደራሽነትና ማስፋፊያ ደንብና የአነስተኛ ኤርፖርቶች ባለቤትነት፣ ግንባታና አስተዳደር ደንብ ለውይይት አቅርቧል፡፡

የአዲስ አበባን ገጽታ በከፍተኛ ደረጃ የሚቀይር የ29 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክት ተነደፈ

በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጠንሳሽነት የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ በከፍተኛ ደረጃ ይለወጣል የተባለ ግዙፍ ፕሮጀክት ተነደፈ፡፡ ይህ 29 ቢሊዮን ብር ይፈጃል የተባለው ግዙፍ ፕሮጀክት፣ በቅርብ ይፋ እንደሚደረግ የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡