ክረምት በሚበረታበት ወርኀ ነሐሴ ከሚውሉ ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓላት ተርታ የሚሰለፈው ቡሔ የሚባለው ነው፡፡ ልጆችንና ወጣቶች በተለይ አደባባይ ወጥተው በየመንደሩ እየተሽከረከሩ ‹‹ሆያ ሆዬ›› የሚሰኝ ጨዋታቸውን ይጫወቱበታል፡፡

የቱሪዝምን ጽንሰ ሐሳብ ኢትዮጵያ ውስጥ በማስተዋወቅ፣ የኢትዮጵያ ቱሪስት ድርጅት በመመሥረትና በዋና ሥራ አስኪያጅነት ያገለገሉት የአቶ ሀብተ ሥላሴ ታፈሰ ሥርዓተ ቀብር፣ እሑድ ነሐሴ 7 ቀን 2009 ዓ.ም. በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከረፋዱ 5 ሰዓት ይፈጸማል፡፡

ከአንድ ሳምንት በላይ ሲካሄድ የቆየው የለንደኑ 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ (ነሐሴ 7 ቀን 2009 ዓ.ም.) ይጠናቀቃል፡፡ ኢትዮጵያ እስከ ዓርብ ምሽት (ነሐሴ 5 ቀን) ድረስ በነበራት ደረጃ በ1 ወርቅና 2 ብር አምስተኛውን ስፍራ ይዛለች፡፡ 

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ መከሰት አንዱ አጋጣሚ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን ይባሉ በነበረበት በግርማዊት ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመን (1909-1922)፣ በ1916 ዓ.ም. አውሮፓና እስራኤልን መጎብኘታቸው እንደሆነ ይወሳል፡፡

ከሳምንት ያነሰ ዕድሜ የቀረው 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በለንደን ከተማ ይካሄዳል፡፡ የኦሊምፒክና የዓለም ሻምፒዮኖቹን ባለወርቆች ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ አትሌቶች ከፍተኛ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡  

Pages