Skip to main content
x
ለአራት ክልሎች የ60 ሚሊዮን ዶላር  የቤተሰብ ድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

ለአራት ክልሎች የ60 ሚሊዮን ዶላር የቤተሰብ ድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

የአሜሪካው የዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (ዩ. ኤስ. ኤ. አይ. ዲ) ከኬር ኢትዮጵያ፣ ከካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስስና ከግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ጋር በመሆን በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች በሚገኙ 36 ወረዳዎች የሚተገበር የ60 ሚሊዮን ዶላር ፕሮግራም ይፋ አደረገ፡፡

ሊቭሊሁድስ ፎር ሪሲሊየንስ የተባለው ፕሮጀክት ለአምስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ገጠራማ አካካቢዎች የሚኖሩ ቤተሰቦች የመተዳደሪያ ገቢያቸው ምንጭ እንዲያሰፉና ከፕሮዳክቲቭ ሴፍቲ ኔት ፕሮግራም እንዲወጡ የሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡

ይህ ፕሮግራም በአሁኑ ወቅት በፕሮዳክቲቭ ሴፍቲ ኔት 4 ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ቤተሰቦች የቢዝነስ ክህሎትና የፋይናንስ እውቀት ሥልጠና በመስጠት እንዲሁም አነስተኛ ብድር እንዲያገኙ በማድረግ እገዛ ያደርጋል፡፡

ይህ ፕሮግራም የአሜሪካው የዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት ፊድ ዘ ፊዩቸር እንቅስቃሴዎች አንዱ አካል ነው፡፡