Skip to main content
x
ዓመታዊው የሚድሮክ ውድድር

ዓመታዊው የሚድሮክ ውድድር

ለ14ኛ ጊዜ በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎችና ተጋባዥ ተቋማት መካከል የሚከናወነው የስፖርት ውድድር፣ የካቲት 26 ቀን 2009 ዓ.ም. በመቻሬ ሜዳ ኮርፖሬት ሴንተር ግቢ ተጀምሯል፡፡ 25 ኩባንያዎችን በአራት የቴክ ምድብ በመመደብ እንዲሁም 11 ሌሎች ተጋባዥ እህት ኩባንያዎችና ተቋማት ውድድራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ የፍጻሜ ጨዋታዎችን ከወራት በፊት በተመረቀው አዲሱ የወልዲያ ስታዲየም ያደርጋሉ፡፡ ለሦስት ወራት የሚቆየው ውድድሩ የኩባንያዎቹ ሠራተኞች የእርስ በእርስ ግንኙነት ለማጎልበት፣ ጤናማ የኩባንያ የሥራ ሰላም ለማስፈንና አዳዲስ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማበረታታት በማቀድ እንደተዘጋጀ፣ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር አረጋ ይርዳው ተናግረዋል፡፡ ዓመታዊውን ውድድር ዶ/ር አረጋ (ፎቶ) አስጀምረውታል፡፡