Skip to main content
x
የፋርስ ድመት

የፋርስ ድመት


የፋርስ ድመት በአሜሪካ ታዋቂ ከሆኑ የቤት እንስሳት ዝርያዎች ዋነኞቹ ናቸው፡፡ በጠፍጣፋ ፊታቸውና በክብ ጭንቅላታቸው የሚታወቁ ሲሆን፣ እግሮቻቸው አጫጭርና  ፀጉራም ድመቶችም ናቸው፡፡

የፋርስ ድመቶች መጀመርያ መገኛቸው አሁን ኢራን በምትባለው አገር ነው፡፡ በ1660ዎቹ ከአውሮፓ እንደመጡ የሚነገርላቸው እነዚህ ድመቶች፣ አሁን የደረሱበት የዕድገት፣ የፀጉር፣ የፊትና የጭንቅላት ቅርፅ እንዲሁም የእግር እጥረት ከተለያዩ የድመት ዝርያዎች በመዳቀላቸው የመጣ መሆኑን ዳክስተር በድረ ገጹ አሥፍሯል፡፡

የፋርስ ድመቶች ቀይ፣ ጥቁር፣ አመድማ፣ ቸኮሌት፣ ነጭ ቀለም ያላቸው ሲሆን፣ የተደበላለቀ ሆኖ የራሱ ቅርፅ ያለው ቀለም፤ ማለትም ነጠብጣብና መስመር ቅርፅ ያላቸውም አሉ፡፡

እነዚህ ድመቶች ጠፍጣፋ ፊት ቢኖራቸውም፣ ሦስት ዓይነት የፊት ቅርጽ ያላቸው በባህሪያቸው ማኅበራዊ ሕይወት ወዳዶች ሲሆኑ፣ ከሰው ጋር የሚኖሩም ናቸው፡፡ እንደሌሎች የድመት ዝርያዎች ጎጂ አይደሉም፡፡ ለሰው ታማኝ መሆናቸውም ይነገራል፡፡ ሰው ወዳድ የሚባሉት የፋርስ ድመቶች የመኖር ዕድሜያቸው እስከ 12 ዓመት ነው፡፡