Skip to main content
x

ዶሮ በሚጥሚጣ

አስፈላጊ ግብዓቶች

 • 1 የተገነጣጠለ ዶሮ
 • ½ ኩባያ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
 • ½ ኩባያ ማርጋሪን ወይም የቆርቆሮ ዘይት
 • 1 የሻይ ማንኪያ ሚጥሚጣ
 • 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
 • 2 ኩባያ የሞቀ ውኃ
 • 1 የሾርባ ማንኪያ የፉርኖ ዱቄት
 • 1 ½ የሾርባ ማንኪያ ቀዝቃዛ ውኃ
 • 1 ኩባያ እርጎ

     አሠራር

 1. የዶሮውን ሥጋ አጥቦ ድስት ውስጥ ውኃ ጨምሮ ማብሰል፡፡
 2. ሽንኩርቱን በዘይት ማቁላላት፣ የተቁላላውን ሽንኩርት አውጥቶ ከተቁላላበት በቀረው ዘይት የዶሮውን ሥጋ መጥበስ፡፡
 3. ከሚጥሚጣው ጋር ጨውና የፈላ ውኃ አዋህዶ የተቁላላውን ሽንኩርት ጨምሮ የሙቀቱ ኃይል መጠነኛ በሆነ እሳት ላይ ለ30 ደቂቃ ከድኖ ማብሰል፡፡ እስቲበስል እንደ አስፈላጊነቱ በትንሽ በትንሹ ውኃ እየጨመሩ የዶሮው ሥጋ ሲበሰል በማውጣት እንዲቀዘቅዝ መክደኛ ባለው ሳህን ውስጥ ማቆየት፡፡
 4. የቀረውን የዶሮ መረቅና እርጎ ጨምሮ ማፍላት፣ በመጨረሻም የፉርኖ ዱቄቱን በቀዝቃዛ ውኃ በጥብጦ ድስቱ ውስጥ ጨምሮ ወፈር እስኪል ድረስ ማማሰል፡፡ ከዚያም ዶሮው ሥጋ ላይ መገልበጥና ትኩሱን ማቅረብ፡፡

አራት ሰው ይመግባል

-  ደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) ‹‹ባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2003)