Skip to main content
x
ጥልመ ጀርባ ቀበሮ

ጥልመ ጀርባ ቀበሮ

ጥልመ ጀርባ ቀበሮ በብዙ የኢትዮጵያ ሥፍራዎች ይገኛል፡፡ ከታንዛኒያ እስከ ቀይ ባሕር፣ እንዲሁም በሶማሊያ ይገኛል፡፡ በተረፈ በብዙ ሌሎች የአፍሪካ ሥፍራዎች ባይገኝም በደቡባዊ አፍሪካ በሚገኙ አገሮች ይኖራል፡፡

የሚኖሩት ተራ ቀበሮ በበዛባቸው አጫጭር ሳር ባሉባቸው ሥፍራዎች ሳይሆን፣ በደኖች አቅራቢያ ነው፡፡ ግራር በሚበዛበት ሥፍራም ይገኛሉ፡፡ ከደኖች አጠገብ ባሉ ረጃጅም ሳር ባለባቸው ሥፍራዎች፣ ተራ ቀበሮዎችም ሆኑ ባለ ጥቁር ጀርባ ቀበሮዎች ይገኛሉ፡፡

የፀጉራቸው ቀለም ከቀይማ ቡኒ እስከ ቢጫማ ቡኒ ሆኖ፣ በጀርባቸው ላይ እንደኮርቻ የተጋደመ ነጭ ነጭ ያለበት ጥቁር ፀጉር አላቸው፡፡ ጅራታቸው ፀጉራም ሆኖ ጫፉ ጥቁር ነው፡፡ ደረትና ሆዳቸው፣ እስከ አንገታቸው ነጭ ነው፡፡

በምግብ ምርጫቸው ከተራ ቀበሮ ልዩነት የላቸውም፡፡ የሳር አይጥ ባለበት ሥፍራ ዋነኛ ምግባቸው ነው፡፡ የዚህ አይጥ ቁጥር በበጋ ወቅት እጅግ ይጨምራ፡፡ ጀርባ ጥቁር ቀበሮ የበግና የፍየል ግልገሎች ስለሚበላ፣ በብዙ ሰዎች የተጠላ እንስሳ ነው፡፡

  • ሰሎሞን ይርጋ (ዶ/ር) ‹‹አጥቢዎች›› (2000)