Skip to main content
x
ፍሬከናፍር

ፍሬከናፍር

‹‹አገር አቀፍ ምርጫው መረጋጋት ካልታየበት፣ የአገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስተሮችን እምነት በመሸርሸር ለኢኮኖሚው ዕድገት የተቀመጠው ግብ እንዳይሳካ ሊያደርግ ይችላል፡፡››

የኬንያ ግምጃ ቤት ዋና ኃላፊ ካማው ቱጌ፣ በቅርቡ በኬንያ ሊካሔድ ዝግጅት የሚደረግበት አገር አቀፍ ምርጫ በኢኮኖሚው ላይ ሊሳድር ስለሚችለው ሥጋት ከተናገሩት የተቀነጨበ ንግግራቸው የተወሰደ ነው፡፡ ኬንያ ለምርጫ ከ500 ሚሊዮን ዶላር ያላነሰ ገንዘብ በመመደቧም ‹‹ውዱ የምሥራቅ አፍሪካ ምርጫ›› ሊያደርገው እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡ በአንጻሩ ሩዋንዳም ከጥቂት ጊዜ በኋላ አገር አቀፍ ምርጫ የምታስተናግድ ሲሆን የመደበችው ወጪ ግን 6.9 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ተሰምቷል፡፡