Skip to main content
x
‹‹የኢትዮጵያ ቀን›› በእንቁጣጣሽ ዋዜማ

‹‹የኢትዮጵያ ቀን›› በእንቁጣጣሽ ዋዜማ

‹‹የኢትዮጵያ ቀን›› የ2010 የአዲስ ዓመት መቀበያ ዝግጅት የተከናወኑና በመከናወን ላይ ያሉ ዝግጅቶች ማጠቃለያ ጳጉሜን 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚሌኒየም አዳራሽ ‹‹እኛ ኢትዮጵያውያን የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌት ነን›› በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ይካሄዳል።

***

‹‹የልብ ሽበት…››

ከፈረንሣይኛና ከሌሎች ቋንቋዎች የተመለሱ 24 አጫጭር ልቦለዶች ለኅትመት በቁ፡ ‹‹የልብ ሽበት እና ሌሎችም›› የሚል ርዕስ ያለው መድበል በኃይላይ ገብረእግዚአብሔር የተዘጋጀ ነው፡፡

በአጫጭር የልቦለድ ድርሰቶች በ19ኛውና 20ኛው ምታመት ዝናን ካተረፉ ጸሐፊዎች አንዱ የሆነው የፈረንሣዊው ጌ ደሞፓሳ፣ የልቦለድ ጸሐፊና ጋዜጠኛ የነበረው የጣሊያናዊው የአልቤርቶ ሞራቪያ፣ የኩምክና እና ቀልድ ጸሐፊና አዘጋጅ የነበረው የፈረንሣዊው ረኔ ጎሲኒ ሥራዎች በመድበሉ ተተርጉመው ቀርበዋል፡፡ የመድበሉ ዋጋ 68 ብር ነው፡፡